ዩ.ኤ.ኢ በሃገሯ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ችግር ለመፍታት ቃል ገባች
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሼክ መሀመድ ቢን ረሺድ አልመክቱም ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዢ ከሆኑት ሼክ መሀመድ ቢን ረሺድ አልመክቱም ጋር ተወያይዩ።
ኢትዮጵያን ለመለወጥ እና በሃገሪቱ ብሎም በአፍሪካ ሰላም ለማስፈን የሚያደረገውን ጥረት ያደነቁት ሼክ መሀመድ ጥረቱን እንደሚደግፉም በውይይቱ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው ትናንትና ከኢትዮጵያውያን የማኅበረሰብ ተወካዮች እና አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ከስራ ፈቃድ፣የአምልኮና የትምህርት ቤት ግንባታ ቦታዎችን ከማግኘት እና ከሌሎችም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች እንደቀረቡላቸው ያነሱ ሲሆን ጥያቄዎቹ መፍትሄ ሊያገኙ ስለሚችሉበት ሁኔታ ተወያይተዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከልዩ ልዩ ኃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩ ቃል የገቡት ሼክ መሀመድም በአቡዳቢ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚሆን ቦታ መፍቀዳቸውን አስታውቀዋል፡፡