የ2025 ምርጥ 10 የዓለማችን ዩንቨርስቲዎች የትኞቹ ናቸው?
የእንግሊዙ ኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ የዓለማችን ምርጡ ዩንቨርሲቲ ተብሏል
የደቡብ አፍሪካው ዊትዋተርስራንድ ዩንቨርሲቲ ከአፍሪካ ቀዳሚው ሆኗል
የ2025 ምርጥ 10 የዓለማችን ዩንቨርስቲዎች የትኞቹ ናቸው?
የዓለማችን ዩንቨርሲቲዎችን በሚቀበሉት ተማሪዎች ብዛት፣ በሚያሳትሟቸው አዲስ ምርምሮች፣ በምሁራን ቁጥር እና ሌሎች መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ የዩንቨርሲቲዎች ደረጃ ይወጣል፡፡
ታየምስ ኦፍ ሀይር ኢዱኬሽን የተሰኘው ተቋም የ2025 የዓለማችን ዩንቨርሲቲዎችን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን የብሪታንያ እና አሜሪካ ዩንቨርሲቲዎች ከ1 እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረዋል፡፡
ኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ ፣ ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ሀርቫርድ ዩንቨርስቲ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረዋል፡፡
ከአፍሪካ ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ዩንቨርሲቲዎች ቀዳሚ ሲሆኑ ዊትዋተርስራንድ ዩንቨርሲቲ እና ጆሀንስበርግ ዩንቨርሲቲ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ሲያዙ የታንዛኒያው መሂምብሊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ደግሞ ቦስተኛ ደረጃ ለይ ተቀምጧል፡፡
የኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች በዚህ ግምገማ መሰረት በምርጥ 30 የአፍሪካ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ ቀርተዋል፡፡