የዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርሲቲዎች እነማን ናቸው?
ሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ ደረጃውን በማሻሻል የዓለማችን ምርጥ ዩንቨርሲቲ ሆኗል
ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ፣ ጎንደር እና መቀሌ ዩንቨርሲቲዎች ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል
የዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርሲቲዎች እነማን ናቸው?
ዓለም አቀፉ የዩንቨርሲቲዎች ደረጃ መዳቢ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎችን ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት ሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ ምርጥ 1ኛ ዩንቨርሲቲ ሲባል ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ስታንፎርድ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዩንቨርሲቲዎች ተብለዋል፡፡
ከአፍሪካ ከአንድ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ የደቡብ አፍሪካ ዩንቨርሲቲዎች ሲቆጣጠሩ ኬፕታወን ዩንቨርሲቲ፣ ዊትዋተርስራንድ ዩንቨርሲቲ እና ስቴለንስቦስች ዩንቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ስድስት ዩንቨርሲቲዎች ከዓለማችን ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሲሆን አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ባህርዳር እ ሐሮማያ ዩንቨርሲቲዎች ተካተዋል፡፡
አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ከአፍሪካ በ841ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ጎንደር ዩንቨርሲቲ በ1701ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቀሌ ዩንቨርሲቲ ደግሞ በ1748ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ግብጽ 20 ዩንቨርሲቲዎቿ በዓለማችን ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ ሲካተቱ ናይጀሪያ 5፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዩንቨርሲቲዎችን ያስመረጡ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ናቸው፡፡
ማዕከሉ የዩንቨርሲቲዎቹን ደረጃ ያወጣው ዩንቨርሲቲዎች በሚያካሂዷቸው ጥናት እና ምርምሮች፣ ትምህርት አሰጣጥ ጥራት፣ የፋኩልቲ አወቃቀሮች እና የሰው ሀይል ጥራት ዋነኛ መስፈርቶች ናቸው፡፡