ፖለቲካ
የዘንድሮው የዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርስቲዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ
የአሜሪካው ማሳቹስቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ12ኛ ጊዜ የዓለማችን ምርጡ ዩንቨርስቲ ሆኖ ተመረጠ
የአሜሪካ እና አውሮፓ ዩንቨርስቲዎች ዘንድሮም ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል
የዘንድሮው የዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርስቲዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ።
ከ240 ሺህ በላይ ምሁራን የተሳተፉበት የ2024 የዓለማችን ዩንቨርሲቲዎች ደረጃ ይፋ ሆኗል።
በዚህ ሪፖርት መሰረት ከዓለማችን አስር ምርጥ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ አምስቱ በአውሮፓ ሲገኙ አንድ ከእስያ ቀሪዎቹ ደግሞ ከአሜሪካ ሆነዋል።
በዘንድሮው ደረጃ መሰረት የአሜሪካው ማሳቹስቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ12ኛ ጊዜ የዓለማችን ምርጡ ዩንቨርስቲ ሆኖ ተመርጣል።
በመቀጠል ደግሞ የእንግሊዞቹ ካምብሪጅ እና ኦክስፎርድ ዩንቨርስቲዎች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ሲይዙ የአሜሪካዎቹ ሀርቫርድ እና ስታንፎርድ ዩንቨርሲቲዎች አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
የዩንቨርስቲዎቹ ደረጃ የተሰጠው በሚያሳትሙት አዲስ እና ችግር ፈቺ ምርምር፣ ባላቸው የምሁራን ጥራት እና ብዛት እንዲሁም በተማሪዎቻቸው ውጤታማነት መሰረት ነው ተብሏል።
የስዊዘርላንዱ ዙሪኩ ዩንቩርሲቲ እና የሲንጋፖር ዩንቨርሲቲ ዎች ከዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርሲቲዎች መካከል ተጠቅሰዋል።