ፖለቲካ
በትራምፕ ፖሊሲ የተለያዩ ህጻናት እና ወላጆች እንዲገናኙ ጆ ባይደን ፈቀዱ
እስካሁን ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ እስከ 700 ህጻናትን ለማገናኘት ታስክ ፎርስ ይቋቋማል
በትራምፕ ፖሊሲ ከ2017 እስከ 2018 (እ.ኤ.አ) በትንሹ 5,500 ህጻናት ከወላጆቻቸው እንዲለዩ ተደርገዋል
በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ2018 'ምህረት የለሽ' ፖሊሲ በሜክሲኮ ድንበር አካባቢ እንዲለያዩ የተደረጉ ስደተኛ ወላጆች እና ልጆቻቸው ዳግም መገናኘት እንዲችሉ አዲሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈቅደዋል፡፡
በሜክሲኮ ድንበር በኩል የሚገቡ ስደተኞችን በተመለከተ የወጣው የትራምፕ ፖሊሲ ተገምግሞ እንዲከለስም ፕሬዝዳንት ባይደን ወስነዋል፡፡
ሕጉን ከፈረሙ በኋላ ባይደን “ሕጻናትን ከቤተሰቦቻቸው እቅፍ እንዲነጠቁ የሚያደርገውን የቀድሞው አስተዳደር ሞራላዊ እና ብሔራዊ አሳፋሪ ተግባር ለመቀልበስ እንሰራለን” ብለዋል ሜትሮ እንደዘገበው፡፡
የባይደንን ውሳኔ ተከትሎ እስካሁን ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ ከ600 እስከ 700 ህጻናትን ለማገናኘት ታስክ ፎርስ ይቋቋማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በትራምፕ ፖሊሲ ከ2017 እስከ 2018 (እ.ኤ.አ) በትንሹ 5,500 ህጻናት ከወላጆቻቸው እንዲለዩ ተደርገዋል፡፡ ይህም በወቅቱ ከፍተኛ አነጋጋሪ እና ብዙዎችን ያሳዘነ ድርጊት ነበር፡፡