ባይደንና የኔቶ ዋና ጸሐፊ በዩክሬን ጉዳይ መወያየታቸውን ጽ/ቤታቸው አስታውቋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የስዊድንና ፊንላንድ ኔቶ የመቀላቀል ሂደት እንዲፋጠን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።
ጆ ባይደን፤ ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ ጋር በኋይት ሃውስ በተወያዩበት ወቅት ሀገራቱ ኔቶን ለመቀላቀል ያቀረቡትን ሃሳብ በበጎ እንደሚመለከቱትም ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት የኔቶ አባል እንዲሆኑ በሚደረገው ሂደት ዋና ጸሐፊው ስቶልተንበርግን እንደሚግዙ የገለጹት ባይደን የሀገራቱ ወደ ድርጅቱ መቀላቀል ጥሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ጆ ባይደንና የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጀንስ ስቶልተንበርግ፤ ተቋሙን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ ሰኔ 29 እና 30 ቀን በስፔን መዲና ማድሪድ ከተማ ስለሚካሄደው የኔቶ ጉባዔም መነጋገራቸው ተሰምቷል።
የአሜሪካ እና የኔቶ መሪዎች በዩክሬን ወቅታዊ ሁኔታና በትራንስ አትላንቲክ የጸጥታ ጉዳች ዙሪያ እንዲሁም ተቋሙን በማጠናከርና የቅድመ መከላከል አቅሙን በማሳደግ ዙሪያ ተነጋግረዋ ተብሏል።
ኔቶ፤ ከአየር ንብረት ለውጥ እስከ ሳይበር ያሉትን ፈተናዎች በሚገባ መመለስ እንዲያስችለው በጀት እንዲኖረው ማድረግ ይገባል ተብሏል።
ዋና ጸሐፊው ከጆ ባይደን በተጨማሪም ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስንና የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫንን ማግኘታቸው ተገልጿል።
ስዊድን እና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን እንዳይቀላቀሉ ሩሲያ ስታስጠነቅቅ ብትቆይም አሜሪካ ግን እደግፋለሁ እያለች ነው። ቱርክ በበኩሏ ሀገራቱ ኔቶን እንዲቀላቀሉ እንደማትፈልግ ገልጻ ነበር።
ከሩሲያ ጋር 1 ሺ 300 ኪሎ ሜትር የምትዋሰነው ፊንላንድ እንዲሁም ፊንላንድ ተቋሙን ለመቀላቀል ጥረት እያደረጉ መሆኑ በአካባቢው ሌላ ውጥረት እንዳያስነሳ እየተሰጋ ነው።