ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ኔቶን “ደካማ ተቋም” ነው ሲሉ ተችተዋል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ነቶ) ን ላትቀላቀል እንደምትችል ማወቅ “ይገባታል” አሉ።
ከሩሲያ ጋር ውጊያ ውስጥ ያስገባቸው ዋነኛ ጉዳይ ኔቶን የመቀላቀል ሃሳብ የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ግን አሁን ተስፋ እየቆረጡ ይመስላል እየተባለ ነው። ኪቭም ኔቶን ላትቀላቀል እንደምትችል መገንዘብ አለባት ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል።
ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ለሩሲያ ብሔራዊ ደህንነት ስጋት እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። ሞስኮ እና ኪቭን ጦርነት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ ምክንያት የሆናቸውም የዩክሬን ኔቶን የመቀላቀል ሃሳብ ነበር።
ኔቶ ግን በሁለቱ ሀገራት ጦርነት ውስጥ እንደማይገባ በዋና ጸሐፊው ጀንስ ስቶልተንበርግ በኩል አስታውቋል።
ኔቶ ግን በሁለቱ ሀገራት ጦርነት ውስጥ እንደማይገባ ማሳወቁን ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ኔቶን “ደካማ ተቋም” ነው ሲሉ መተቸታቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ኔቶ የዩክሬንን ቀጠና ከበረራ ነጻ ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን ከገለጸ በኋላም ነበር፡፡
ዩክሬን የኔቶ አባል ሀገራት አለመሆኗን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ “ድርጅቱን ለመቀላቀል በሩ ክፍት ነው ስንባል የቆየን ቢሆንም አሁን አባል መሆን እንደማንችል ሰምተናል” ብለዋል።
አሁን ላይ የዩክሬን ሕዝብ ይህንን ሀቅ በመረዳት በራሱ ላይ እና እየረዱት ባሉት ወዳጆቹ ላይ እየተማመነ በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።
ዩክሬን እና ሩሲያ ወደ ጦርነት ካመሩ ዛሬ 21 ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን ጦርነቱን ተከትሎም እስካሁን ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዩክሬናውያን ሀገራቸውን ጥለው ተሰደዋል።
ርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 20 ህጻናትን ጨምሮ 364 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል።