የዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል ማቀድ ከሩሲያ ጋር ጦር እያማዘዘ ነው
የፊንላንድ መሪዎች ሀገሪቱ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ን እንድትቀላቀል መወሰናቸውን አስታወቁ።
ሀገሪቱ የኔቶ አባል እንድትሆን ድጋፍ የሰጡት የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት ናቸው።
ፕሬዝዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን በጋራ ባወጡት መግለጫ ፊንላንድ በአስቸኳይ የኔቶ አባል እንድትሆን ማመለከቻ ማስገባት አለባት ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ፕሬዝዳንቱ በጋራ መግለጫቸው የፊንላንድ ኔቶን መቀላቀል የጸጥታ ሁኔታዋን ያጠናክርላታል ብለዋል።
ሀገሪቱ የኔቶ አባል ስትሆን ኔቶም እንደሚጠናከር ነው የተገለጸው። ፊንላንድን የኔቶ አባል ለማድረግ የሚደረገው ብሄራዊ ሂደት መፋጠን እንዳለበትና በቅርብ ቀናት ማለቅ እንዳለበት ተገልጿል።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)28 የአውሮፓ ሀገራት፤ አሜሪካ እና ካናዳን ጨምሮ በድምሩ 30 አባል ሀገራት ያሉት የጋራ የመከላከያ ተቋም ነው።
መቀመጫውን በቤልጄም ብራሰልስ ያደረገው ተቋሙ አሁን ላይ 34ኛ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት ጀንስ ስቶልተንበርግ እየተመራ ይገኛል።
የኔቶ መስራቾች ከሆኑት ሀገራት መካከል አሜሪካ፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይና ጣሊያን ይገኙበታል። የተለያዩ ሀገራት አሁን ላይ ኔቶን ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የዩክሬን ድርጅቱን ለመቀላቀል ማቀዷ ከሩሲያ ጋር ጦር እያማዘዛት ነው።
ይህንን ተከትሎም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ኔቶን “ደካማ ተቋም ነው” ማለታቸው ይታወሳል።