በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር ትራምፕ በባይደን ላይ የበላይነትን ተቀዳጅተዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከምርጫ 2024 ዘመቻ ራሳቸውን እንዲያገሉ ከዴሞክራች እየቀረበባቸው ያለውን ግፊት ውድቅ አደረጉ።
ባይደን ከምርጫው ራሳቸውን እንዲያገሉ የሚሉ ጥያቄዎች እየበረቱ የመጡት ፕሬዛዳንቱ ባሳለፍነው ሳምንት ከሪፐብሊካኑ ተፎካሪያቸው ጋር በነበራቸው የፊትለፊት ክርክር ላይ ያሳዩትን ደካማ አቋም ተከትሎ ነው።
በምርጫ ክርክሩ ላይ ፕሬዝዳንት ባይደን አቅማቸውንና አለመድከማቸውን ሊያሳዩ፤ ገና ሌላ የስልጣን ዘመንን የመምራት አካላዊና አእምሯዊ ብቃት እንዳላቸው ሊያስመሰክሩ ነበር ያለሙት ።
ሆኖም ግን ጆ ባይደን በ2024 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ የመጀመሪያው የቴሌቭዥን ክርክር የ90-ደቂቃ ፍልሚያ ላይ ደካማ አፈጻጸም አሳይቷል ነው የተባለው።
ጆ ባይደን ድምጻቸው ደክሞ፣ በራስ መተማመናቸው ጠፍቶ፣ አቀርቅረው፣ ሃሳባቸው ተበትኖና አንደበታቸው ተሳስሮ ነበር ክርክሩን የጨረሱት።
በክርክሩ ማብቂያ ላይ በተሰበሰበ የህዝብ አስተያየት ትራምፕ 67 በመቶ ባይደን ደግሞ 33 በመቶ ድምጽ በማግኘታቸው ትራምፕ ክርክሩን በሰፊ ልዩነት ማሸነፋቸውን አሳይተዋል።
ዴሞክራቶች በፕሬዚዳንቱ አፈጻጸም ላይ ስጋታቸውን ገልጸዋል የተባለ ሲሆን፤ የፓርቲው የውስጥ አዋቂዎች ቀደም ሲል የሰጡት መልሶች ፍርሃትን እንዳጫረባቸው ተናግረዋል።
ይህንን ተከትሎም ዴሞክራቶች የሕግ አውጭዎች እና ገዥዎች ባይደን ባሳለፍነው ሳምንት ክርክር ላይ ያሳዩትን ደካማ አፈጻም ተከትሎ የምርጫ ዘመቻቸውን እንዲያቋርጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ባይደን የቀረበላቸውን ጥሪ ተከትሎም በሰጡት አስተያየት፤ “ማንም ሰው ገፍቶ ሊያስወጣኝ አይችልም፤ የማቋርጠው ነገር የለም፤ እዚህ ሩጫ ውስጥ የገባሁት እስከ ፍጻው ለመቆየት ነው ብለዋል።
የዴሞክራ እጩ ጆ ባይደን በምርጫው 'እስከ መጨረሻው' ለመታገል ቃል ገብቷል።