በፎርብስ የቢሊየነሮች ደረጃ መሰረት ፈረንሳዊው በርናርድ አርኖልት የአለማችን ቁጥር 1 ቱጃር ሆነዋል
በአለም አቀፍ ደረጃ 2 ሺህ 640 ቢሊየነሮች አሉ።
በፎርብስ የቢሊየነሮች ደረጃ እስከ 25ኛ የተቀመጡት ቢሊየነሮች አጠቃላይ ሀብትም 2 ነጥብ 1 ትሪሊየን ዶላር መድረሱ ተመላክቷል።
በ2023 የእነዚህ ባለጠጎች ሃብት ባለፈው አመት ከነበረበት የ200 ቢሊየን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱንም ነው ፎርብስ የጠቀሰው።
እንደ አማዞን ባለቤቱ ጄፍ ቤዞስ ሃብቱ የቀነሰ ግን የለም፤ 38 ከመቶ ሃብቱን (57 ቢሊየንን ዶላር) አጥቆ ባለፈው አመት ይዞት ከነበረው ሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ዝቅ ብሏል።
ትዊተርን በ44 ቢሊየን ዶላር የገዛው ኤለን መስክም የሃብት መጠኑ በ39 ቢሊየን ዶላር ቀንሶ የአለማችን ቀዳሚው ቱጃርነቱን ለፈረንሳዊው በርናርድ አርኖልት አስረክቧል።
የ2023 የአለም 10 ባለጠጎች ዝርዝር እና የሃብት መጠናቸውን ይመልከቱ