በህዳር 6 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር ስንት ብር ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 122 ብር ገዝተው እስከ 125 ብር እየሸጡ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ በትናትናው እለት የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ እና መሸጫ ዋጋው ላይ የሁለት ብር ጭማሪ አድርጓል። በዚህም በዛሬ ህዳር 6 2017 ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን፤ አንድ ዶላርን በ122.8506 ብር እየገዛ በ125.3076 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ እለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ላይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ማሻሻያ አላደረገም። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ብርሃን ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.5630 ብር እየገዛ በ123.9943 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
ንብ ባንክ ከሁለት ከሰሞኑ ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል፤ በዚህም አንድ ዶላርን በ120.4610 ብር እየገዛ በ122.8702 ብር እየሸጠ ነው።