የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ የህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ እና መሸጫ ዋጋው ላይ የሁለት ብር ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ ዶላርን በ122.8506 ብር እየገዛ በ125.3076 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ብርሃን ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.5626 ብር እየገዛ በ123.9939 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
አቢሲኒያ ባንክ እለታዊ የውጭምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ከትንናቱ የሳንቲሞች ጭማሪ አድርጓል።በዚህም አንድ ዶላርን በ120.6001 ብር እየገዛ በ123.0121 ብር እየሸጠ ነው።