በህዳር 2 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር ስንት ብር ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 121 ብር ገዝተው እስከ 123 ብር እየሸጡ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባለፈው ሳምንት የውጭ ምንዛሬ ተመኑን አስቀጥሏል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጎህ ቤቶች ባንክ አንድ ዶላር በ121.5204 ብር ገዝቶ በ123.9508 ብር እየሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
ኦሮሚያ ባንክ እለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ላይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ማሻሻያ አላደረገም። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ጸደይ ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ120.9073 ብር እየገዛ በ123.3255 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
ዳሽን ባንክ የህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ እና መሸጫ ዋጋው ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ ዶላርን በ120.8506 ብር እየገዛ በ123.2676 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
አቢሲኒያ ባንክ ከሁለት ቀናት በፊት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል፤ በዚህም አንድ ዶላርን በ120.5001 ብር እየገዛ በ122.9101 ብር እየሸጠ ነው።