የምናባዊ ገንዘብ መገበያያ ገንዘቦች ከሚያዚያ ጀምሮ በታሪክ ከፍተኛ ምንዛሬ ዋጋ እንደሚያገኙ እየተገመተ ይገኛል
አንድ ቢትኮይን በ59 ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ዋጋው አሽቆልቁሎ የነበረው የዓለም ምናባዊ ወይም ክሊፕቶከረንሲ መገበያያ ገንዘብ ከፍተኛ ጭማሪ በመሳየት ላይ ይገኛል።
አሁን ላይ እንድ ቢትኮይን በ59 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ እንደሆነ እና ጭማሪው ከ202 ወዲህ በታሪክ ከፍተኛው ጭማሪ እንዳሳየ ፎርብስ ዘግቧል፡፡
የቢትኮይን ዋጋ በተከታታይ ጭማሪ ያሳየው አሜሪካ በምናባዊ መገበያያ ገንዘብ አክስዮን መሸጥ እና መግዛት እንደሚቻል ከፈቀደች በኋላ ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሺዎች ጭማሪ አሳይቷል።
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ጭማሪ የፈረንጆቹ 2024 ከገባ በኋላ ብቻ የ33 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር ሊመዘር እንደሚችል ተገለጸ
ባሳለፍነው ሰኞም በአሜሪካ ብቻ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር እለታዊ ግብይት እንደተፈጸመት ሲገለጽ ይህም በታሪክ ከምናባዊ ገንዘቦች ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡
የምናባዊ ግብይት ፍላጎት በየጊዜው እየጨመረ ሲሆን በዓለማችን በየቀኑ በአማካኝ 90 ቢሊዮን ዶላር በምናባዊ ገንዘቦች ግብይት በመፈጸም ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዓለማችን ቀዳሚ የሆነው የምናባዊ መገበያያ ገንዘብ ቢትኮይን የተሰኘው ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው ከ12 ዓመት በፊት ሲሆን የአንዱ ቢትኮይን ዋጋም 12 ዶላር ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ማንኛውንም ምናባዊ መገበያያ ገንዘብ በይፋ ያገደች ሲሆን ለዚህ ግብይት የሚረዱ መሰረተ ልማት አልሚ ኩባንያዎች ግን ወደ ስራ እንዲገቡ ፈቃድ በመስጠት ላይ ትገኛለች፡፡
እስካሁን በተደረገው ጥረትም 25 የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደወሰዱም ተገልጿል፡፡