
ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ የመብት ተሟጋች ጆን ለዊስ በ80 አመታቸው አረፉ
ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ የመብት ተሟጋች ጆን ለዊስ በ80 አመታቸው አረፉ
ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ የመብት ተሟጋችና የኮንግረስ አባል የሆኑት ጆን ለዊስ በ80 አመታቸው አርፈዋል፡፡ የጆን ለዊስ ሞት ተከትሎ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ ታዋቂ አሜሪካውያን ሀዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
ባራክ ኦባማ ጆን ለዊስ ሀገሩን ይወድ ነበር፤ ህይወቱን አደጋ ላይ በመጣል እቅዱን ለማሳካት የጣረ ነበር ብለዋል፡፡ እናም በአስርት አመታት በሚቆጠረው ጊዜ ውስጥ ህይወቱን ብቻ ለፍትህና ለነጻነት መስጠቱ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች እሱን ምሳሌ አድርገው እንዲንቀሳቀሱ አስችሏቸዋል ብለዋል፡፡
የቀድሚው ፕሬዘዳንት ቢል ክሊንተንናየቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በጋራ ባወጡት መግለጫ ለእኩልነትና ለነጻነት ያለውን ሁሉ የሰጠውን ታላቅ ሰው በማጣታቸው እንዳዘኑ ገልጸዋል፡፡
ጆን ለዊስ ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር በመሆን ለጥቁር አሜሪካውያን እኩልነት የታገለ የመብት ተሟጋች ነበር፡፡