የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ዋና መስሪያቤቱን በጥቁር አሜሪካዊት ኢንጂነር ስም ለመሰየም ወሰነ
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ዋና መስሪያቤቱን በጥቁር አሜሪካዊት ኢንጂነር ስም ለመሰየም ወሰነ
የአሜሪካው ብሔራዊ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ በተቋሙ ከፍተኛ ሚና የነበረባቸውን አፈሪካ አሜሪካዊት ኢንጂነር ለማሰብና ለመዘከር በሚል የዋና መስሪያ ቤቱን ስም በእርሳቸው ስም አደረገ፡፡
በዚህ መሰረትም የናሳ ዋና መስሪያ ቤት ከዚህ በኋላ ሜሪ ጃክሰን ተብሎ እንዲሰየም መወሰኑን የናሳ አስተዳዳሪ ጂም ብሪድን ሰቲን ይፋ አድርገዋል፡፡
ሜሪ ጃክሰን የአሜሪካ ጠፈርተኞች ወደ ሕዋ እንዲበሩ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከነበራቸው ሳይንቲስቶች መካከል ግንባር ቀደም በመሆና ተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ስያሜ በእርሳቸው ስም እንዲሆን ተወስኗል ነው የተባለው፡፡
አፍሪካ አሜሪካውያን በምህንድስና እና በቴክኖሎጅ ዘርፎች በስፋት እንዲሰማሩ ፈተናዎችን በማለፍ እና ዕድሎችን በማመቻቸት በኩል አርአያ እንደነበሩም ነው የተገለጸው፡፡
ይህንን በዋሸንግተን ዲሲ የሚገኘውን አዲሱን የናሳ ቢሮ በጃክሰን ስም መሰየሙንን ይፋ ሲደረግ ትልቅ ኩራት ይሰማናል ብለዋል የናሳ ኃላፊዎች፡፡ በናሳ ውስጥ የሚመራመሩ አፍሪካ አሜሪካውያን ሴቶች ላይ ያተኮረው “ሂድን ፊገር” የተሰኘ መጽሀፍና ፊልም እንዲተዋወቅ ከፍተኛ ሚና መስራቷም ነው የተጠቀሰው፡፡
ጃክሰን የሴት ተመራማሪዎች በናሳ ውስጥ የሚደርስባቸውን ጫና እንዲነሳ ለማድረግ ፕሮግራሞችን መምራቷም ተጠቅሷል፡፡ ከተቋሙ በአውሮፓውያኑ 1985 ላይ ጡረታ የወጣችው ጃክሰን በ83 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡
የናሳ አስተዳዳሪ ከዚህ በኋላ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሴቶችን እና አፍሪካ አሜሪካውያንን ዕውቅና እንሰጣለን፣መደበቅ የለም ብለዋል፡፡ይህ ውሳኔ የተላለፈው ከጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ሞት በኋላ ነው፡፡