በዚህ ቦታ የሚቀጣጠሩ አጋር ፈላጊዎች ሴቶች ወንዱን ሙሉ አካል ማየት የሚያስችል ሲሆን ሴቷ ግን በከፊል ብቻ ማሳየቱ ቁጣን ቀስቅሷል
ወንዶች ብቻ ወጪ እንዲከፍሉ የሚገደዱበት ካፍቴሪያ
ከሰሞኑ በቬትናሟ ሆቺሚኒ ከተማ አዲስ የተከፈተ አንድ ካፌ አለ፡፡ ሚና ካፌ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ይህ ካፌ የፍቅር አጋር ለሚፈልጉ ሰዎች በሚል እንደተከፈተ ተገልጿል፡፡
ይህ ካፌ የፍቅር አጋር የሚፈልጉ ሰዎች ወደ ካፍቴሪያው ከገቡ በኋላ የወንድ እና ሴት መቀመጫ ወንበሮች ተዘጋጅተዋል፡፡
እነዚህ ወንበሮች ወንዱ ሴቷን በሚገባ ማየት እንዲችል የተዘጋጀ ሲሆን በአንጻሩ ግን ሴቷ ወንዱን ሙሉ ለሙሉ ማየት እንዳትችል በሚከለክል መልኩ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የዚህ ካፌ ሌላኛው ህግ ወጪውን ሙሉ ለሙሉ ወንዱ ብቻ እንዲከፍልም ያስገድዳል፡፡
ካፍቴሪያው የፍቅር አጋር ለሚፈልጉ ጥሩ አማራጭ ቢሆንም የካፌው ህግ ግን ተጠቃሚዎችን እንዳበሳጨ በቬትናም ማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል፡፡
የካፍቴሪያው ባለቤት እንዳለችው ጉዳዩ በሀገሪቱ ዋነኛ መነጋገሪያ ይሆናል ብላ እንዳልጠበቀች በርካታ አስተያየቶች እየደረሷት እንደሆነም ተናግራለች ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በካፌው የፌስቡክ ገጽ አሉታዊ አስተያየቶች መብዛታቸውን ተከትሎም ገጹን ለመዝጋት እንደተደደችም አስታውቃለች፡፡
በካፌው ላይ እየቀረቡ ባሉት አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያት ስራዋን እንደማታቆም የገለጸችው ይህች የካፌው ባለቤት የተጣሰ ህግ የለም ስራዬን እቀጥላለሁ ብላላች፡፡