የሩሲያ ሰላዩ ነጭ አሳ ነባሪ በስዊድን ወደብ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኗል
ይህ አሳነባሪ ከአራት ዓመት በፊት መታየቱ የዲፕሎማሲ መካረር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኖ ነበር
የስዊድን ተመራማሪዎች አሳ ነባሪው ሆን ተብሎ የሆርሞን ለውጥ እንዲታይበት ሳይደረግ እንዳልቀረ
ሩሲያ አሰልጥና እንዳሰማራችው የሚጠረጠረው ነጩ አሳ ነባሪ በስዊድን ወደብ ታየ።
የሩሲያ የስለላ ተቋማ ግሪንላንድ እና አካባቢው ላይ ያለውን የባህር ላይ እንቅስቃሴ ለመሰለል ትጠቀምበታለች ይባላል ይህን ነጭ አሳ ነባሪ።
ይህ አሳ ነባሪ ከሌሎች የአሳ ነባሪ ዝርያዎች ጋር ሲንቀሳቀስ ዝቅተኛ እንቅስቃሴ ማድረጉ ለሩሲያ መጠርጠር ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
የፓስፊክ እና አትላንቲክ ዊቂያኖስ በአቋራጭ ለመጓዝ ይጠቅማል የተባለው የአርክቲክ ባህር ሩሲያ መቆጣጠር እንደምትፈልግ ይገለጻል።
ለዚህ ፍላጎቷም አንድ ነጭ አሳነባሪን በማሰልጠን እና የሆርሞን እንቅስቃሴዎችን መቆጣጠር የሚያስችል ድርጊት ሩሲያ እንደፈጸመችም በስዊድን እና ኖርዌይ ዘንድ ትጠረጠራለች።
ይህ አነጋጋሪ ነጭ አሳ ነባሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 2019 ላይ ታይቶ የነበረ ቢሆንም ከሰሞኑ ደግሞ በስዊድኑ ባረንት ወደብ ለትንሽ ጊዜ ታይቶ መልሶ ሙሰወሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
አሳ ነባሪው ከዚህ በፊት ከነበረው እንቅስቃሴ በተለየ መንገድ ፈጣን እንቅስቃሴ ማድረጉ ሩሲያ የአሳ ነባሪውን ሆርሞን ሳትቀይረው እንዳልቀረች በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
የባህር ላይ እንስሳት ተመራማሪው ሴባስቲያን ስትራንድ በበኩላቸው አሳ ነባሪው ወደ እይታ ብቅ ያለው ብቸኝነቱን ለማስወገድ አልያም ፍቅረኛ ፍለጋ ስለመምጣቱ ግምታቸውን ተናግረዋል።
ሩሲያ በአሳ ነባሪው ጉዳይ በኖርዌይ እና ስዊድን ዜጎች ስለቀረበባት ክስ እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጠችም።