የጤና መድህን ክፍያ ለማግኘት ሲል ሁለት እግሮቹን የቆረጠው አነጋጋሪ ሰው
ፖሊስ ጉዳዩን በመጠራጠሩ ባደረገው ምርመራ አደጋው ሆን ተብሎ የተከሰተ አረጋግጧል
የ60 ዓመቱ አሜሪካዊ የጤና መድህን ክፍያ ለማግኘት ሲል እግሮቹን ቢቆርጥም ያሰበውን ገንዘብ ማግኘት አልቻለም
የጤና መድህን ክፍያ ለማግኘት ሲል ሁለት እግሮቹን የቆረጠው አነጋጋሪ ሰው
በአሜሪካዋ ሚዙሪ የሚኖረው ግለሰብ የጤና መድህን ክፍያ ለማግኘት ሲል የወሰደው እርምጃ ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡
የ60 ዓመቱ ይህ ግለሰብ አሰቃቂ አደጋ እንደደረሰበት በማስመሰል የጤና መድህን ክፍያ ለማግኘት የወሰደው እርምጃ በመጨረሻም ራሱን ለባሰ መከራ ዳርጓል፡፡
ግለሰቡ በትራክተር ላይ በሚገጠም ስለታማ ጫፍ ባላቸው ማረሻ እግሮቹ እንዲቆረጡ ያደረገ ሲሆን አደጋው ለብዙዎች ሰቅጣጭ ሆኗል፡፡
በናይጀሪያ ለደህንነቱ የሰጋ ፓስተር ክላሽ ይዞ መስበኩ አነጋጋሪ ሆኗል
እግሮቼ ተቆርጠው ለከፋ አደጋ ተጋልጫለሁ በሚል ለጤና መድህን ክፍያ የጠየቀው ይህ ግለሰብ ድርጅቱ ከፖሊስ ጋር በመተባበር አደጋው እንዴት እንደደረሰበት ባደረገው ማጣራት ግለሰቡ አደጋውን ሆን ብሎ ማድረሱን አረጋግጧል፡፡
ለክፍያ ብሎ ሁለቱንም እግሮቹን ያጣው ይህ ግለሰብ በመጨረሻም ያሰበውን ገንዘብ ሳያገኝ ራሱን ለተደራራቢ እና ስቃይ መዳረጉን ለየት ያሉ የዓለማችን ክስተቶችን የሚዘግበው ኦዲቲ ሴንታራል ዘግቧል፡፡
ፖሊስም ግለሰቡ በሀሰተኛ መንገድ ያልተገባ ክፍያ ለማግኘት የሞከረውን ግለሰብ በወንጀል ከመጠየቅ ይልቅ ህክምናውን ይከታተል ሲል ትቶታል ተብሏል፡፡
የጤና መድህን ኩባንያው በበኩሉ ብዙ አይነት አደጋዎች አይቶ እንደሚያውቅ ነገር ግን እንዲህ አይነት ሰቅጣጭ አደጋ ሪፖርት ደርሶኝ አያውቅም ብሏል፡፡