የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አቅንተዋል
ሚኒስትር እስራኤል እና ዌስትባንክን ጨምሮ ጆርዳንን፣ ኳታርን፣ ሳኡዲ አረቢያን፣ አረብ ኢምሬትስን እና ግብጽን ይጎበኛሉ ተብሏል
ይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለሳምንት የሚቆየው ጉዞ፣ ሀማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሰበት ከፈረንጆቹ ጥቅምት 2023 ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ ነው
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አቅንተዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን በትናንትናው እለት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ማምራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ ወደ መካከለኛ ምስራቅ ያመሩት በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተጀመረው ጦርነት ወደ ቀጣናው ይስፋፋል የሚል ስጋት ባየለበት ወቅት ነው።
ይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለሳምንት የሚቆየው ጉዞ፣ ሀማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ካደረሰበት ከፈረንጆቹ ጥቅምት 2023 ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ ነው።
ሚኒስትር እስራኤል እና ዌስትባንክን ጨምሮ ጆርዳንን፣ ኳታርን፣ ሳኡዲ አረቢያን፣ አረብ ኢምሬትስን እና ግብጽን ይጎበኛሉ ተብሏል።
ከጦርነቱ በኋላ ጋዛ እንዴት መተዳደር አለባት በሚለው አስቸጋሪ ጉዳይ መሻሻል መኖሩን የጠቀሱት ብሊንከን ተጨማሪ የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ብሊንከን ጉዞ ያደረጉት በሀማስ ምክትል የፖለቲካ መሪ ሳለህ አል አሮሪ ላይ የደረሰው ጉድያ፣ ግጭቱን ቀጣናዊ ያደርገዋል የሚል ስጋት ከተፈጠረ በኋላ ነው።
ከእስራኤል ጋር የተኩስ ልውውጥ እያደረገ ያለው በኢራን ይደገፋል የሚባለው የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ ዝቷል።
የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት ወደ ቀይ ባህር ተስፋፍቶ መፋጠጥ ፈጥሯል።
የሀማስ አጋር የሆኑት እና አብዛኛውን የየመን ክፍል የተቆጣጠሩት የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ 20 መርከቦች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።
በጋዛ መጠነሰፊ ጥቃት እያካሄደች ያለው እስራኤል ጦርነቱ ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ገልጻለች።