ኩባንያው ከኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋዎች በኋላ የ35 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል
የቦይንግ ኩባንያ ዓመታዊ ኪሳራ 12 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ።
የዓለማችን ቀዳሚ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው ቦይንግ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ኪሳራ እያስመዘገበ ነው ተብሏል።
በተለይም ቦይንግ ሰራሽ የሆኑ ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢንዶኔዢያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተከስክሰው 346 ሰዎች ከሞቱ በኋላ ኪሳራው መባባሱን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ቦይንግ ከ2019 ጀምሮ የደረሰበት የ35 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል።
ይህ እንዳለ ሆኖ ከአንድ ዓመት በፊት ከኩባንያው ምርቶች መካከል 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች በበረራ ላይ እያሉ የበር እና ሌሎች ምርቶች መገንጠላቸው ኪሳራውን እንዲጨምር አድርጋል ተብሏል።
በቅርቡ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ብቻ ቦይንግ የ12 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ ኪሳራ እንደደረሰበት ተገልጿል።
ኪሳራው የተከሰተው በድርጅቱ ሰራተኞች ስራ ማቆም አድማ፣ የአሜሪካ አቪዬሽን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላንን እንዳያመርት እገዳ መጣሉ፣ የአውሮፕላን ግዢ ትዕዛዞችን በወቅቱ አለማስረከብ እና ሌሎችም በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።
የተቋሙን ኪሳራ ተከትሎ የአንድ ቦይንግ አክስዮን ድርሻ የ5 ዶላር ቅናሽ እንዲያሳም አድርጓል ተብሏል።
በአጠቃላይ ቦይንግ ኩባንያ በ2024 348 አውሮፕላኖችን ሰርቶ ለገዢዎቹ ሲያስረክብ በ2023 528 አውሮፕላኖችን አስረክቦ ነበር።
በአንጻሩ የቦይንግ ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆነው ኤርባስ ኩባንያ በአዳዲስ አውሮፕላን ግዢ፣ በዓመታዊ ትርፍ እና ሌሎች ገቢዎቹ ከፍተኛ ጭማሪ እንዳሳየም ተገልጻል።