ቦይንግ 787 አውሮፕላን የጥራት ችግር እንዳለበት አንድ ውስጥ አዋቂ ሰራተኛ አጋለጠ
ቦይንግ ኩባንያ በበኩሉ በውስጥ አዋቂ ሰራተኛው የተሰነዘረበትን የጥራት ጉድለት ሀሰተኛ ነው ብሏል
ቦይንግ ኩባንያ ከምርት ጥራት ጋር በተያያዘ በየጊዜው የተለያዩ ትችቶችን በማስተናገድ ለይ ነው
ቦይንግ 787 አውሮፕላን የጥራት ችግር እንዳለበት አንድ ውስጥ አዋቂ ሰራተኛ አጋለጠ፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ የአቪዬሽን ኩባንያ የሆነው ቦይንግ ከዚህ በፊት ከ737 ማክስ አውሮፕላን ጋር በተያያዘ የተለያዩ ችግሮችን አስተናግዷል፡፡
ምርቶቹ ላይ የጥራት ችግር እንዳለባቸው በቀድሞ ሰራተኞቹ የተጋለጠው ቦይንግ ኩባንያ በተግባር ደግሞ አውሮፕላኖቹ በበረራ ላይ እያሉ መስተጓጎሎች አጋጥመውታል፡፡
አሁን ደግሞ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ምርቶች በገጠማ ወቅት የጥራት ችግር እንዳለባቸው አንድ ሰራተኛ ይፋ አድርጓል፡፡
ለቦይንግ ኩባንያ የምርት ግብዓት የሚያቀርበው ስፕሪት ኤሮስፔስ ሲስተምስ ኩባንያ ሰራተኛ የሆነው ሪቻርድ ኩቫስ የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን የጥራት ጉድለት ያለባቸው ምርቶችን ተጠቅሟል ብሏል፡፡
እንደ ሰራተኛው አስተያየት በ787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ፊተኛው አካል ላይ የሚገጠም ምርት ችግር እያለበት እና ችግሩ ለቦይንግ ተነግሮት ለማስተካከል ፈቃደኛ አልሆነም ብሏል፡፡
ሰራተኛው በቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ምርት ላይ ያጋጠመውን የምርት ችግር ባሳወቀ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከስራ እንደተባረረም ተናግሯል፡፡
የቦይንግን የጥራት ችግር ያጋለጠው ሁለተኛው ሰው በድንገት ህይወቱ አለፈ
ቦይንግ ኩባንያ በበኩሉ በሰራተኛው የቀረበበትን የጥራት ችግር እንደደረሰው ገልጾ ባደረገው ማጣራት ያጋጠመ ችግር የለም ሲል መናገሩን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ አቪዬሽን ባለስጣን በበኩሉ በቦይንግ ምርቶች ላይ የጥራት ችግር አለ ብለው የሚያስቡ ሰዎች እና ተቋማት የሚሰጧቸውን ጥቆማዎች እንደሚያበረታታ አስታውቋል፡፡
እስካሁን ድረስም በዚህ ዓመት ብቻ በቦይንግ ኩባንያ ላይ 126 ጥቆማዎችን እንደደረሱት እና እየመረመረ መሆን ገልጿል፡፡