ዝነኛው ፊሊፒናዊ ቦክሰኛ “ፓኪዮ” ለፕሬዝዳንትንት ሊወዳደር ነው
ገዢው ፓርቲ “የፕሬዝዳንት ሮድሪጎ የቅርበ ሰው ሴናተር ክሪስቶፈር”ን ለፕሬዝዳንትነት እጩ አድረጎ አቅርቧል
ከሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ ያፈነገጠው አንጃ ፓኪዮን ለ2022 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ አድርጎ አቅርቧል
ፊሊፒናዊው ቦክሰኛ ማኒ ፓኪዮ ለፕሬዚዳንትነት ዕጩ ሆኖ ተመረጠ፡፡
የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ማኒ ፓኪዮ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ መሆን የቻለው አሁን ሀገሪቱን እየመራ ከሚገኘውና በፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ ከሚመራው ፒዲፒ-ላባን ፓርቲ / PDP-Laban party/ ባፈነገጠው አንጃ አማካኝነት በመመረጡ ነው፡፡
በዚህም ፊሊፒንስ እንደፈረኝጆቹ 2022 በምታካሂደው ምርጫ ማኒ ፓኪዮ አንጃውን ወክለው ለፕሬዝዳንትንት እንደሚወዳደሩ የቅርብ ጓደኛው ሴናተር አኩሊኖ ፒሜንቴል “ኮኮ” ማስታወቃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
የአንጃው ቡድን እውቁ ቦክሰኛና ሴናተር ፓኪዮ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ አድርጎ የመረጠው የሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም ሮድሪጎን የረጅም ጊዜ ረዳቱ ሴናተር ክሪስቶፈር “ቦንግ” ለፕሬዝዳንትነት ማጨቱን ተከትሎ ነው፡፡
ፓኪዮ ለፕሬዝዳንትንት የመወዳደሩን ነገር ከዚህ በፊት እንደቀልድ ነበር የሚያነሳው፡፡
ፓኪዮ ቀደም ሲል ሰሶስት አማራጮች አሉኝ እነሱም “ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር፣ እንደገናም ለሴናተርነት ወይም ከፖለቲካ ጡረታ መውጣት ናቸው” ይል ነበር፡፡
ፓኪዮ በ2022 ምርጫ አብረውት የሚወዳደሩ ጓዶቹን ይመርጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል አወዛጋቢው ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት መታጨታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱን ሁለተኛ ቁልፍ ስልጣን ለመወደዳር መወከላቸው ለስልጣን ያላቸው ከፍተኛ ጥማት የሚያመላክት እንደሆነ በርካቶች በመናገር ላይ ናቸው፡፡