በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ ያሉት የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ካረን ባስ ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈጉባዔዎች ጋር ተወያዩ
ፕሬዝዳንት ባይደን በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የቀረበላቸውን የውሳኔ ሃሳብ በፊርማቸው ማጽደቃቸው የሚታወስ ነው
የኮንግረስ አባላቱ ከሌሎች ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውም የሚታወስ ነው
በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ ያሉት የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ካረን ባስ ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈጉባዔዎች ጋር ተወያዩ፡፡
ካረን ባስ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ጋር ነው የተወያዩት፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን በኢትዮጵያ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ማእቀብ እንዲጣል ትእዛዝ አስተላለፉ
በውይይቱ ሌላኛዋ የኮንግረስ አባል ሳራ ጃኮፕስን መገኘታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ሆኖም ውይይቱ በምን ጉዳይ ላይ እንዳተኮረ እና ምን እንደተነሳበት የተገለጸ ነገር የለም፡፡
ካረን ባስ በኮንግረንሱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስር የአፍሪካ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና ሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም የጥቁር አሜሪካውያን ኮንግረስ አባላት ጉባኤ ሰብሳቢም ናቸው።
ሳራ ጃኮፕስ ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጣር ከ2020 ጀምሮ የኮንግረሱ አባል ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
የኮንግረስ አባላቱ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።
ከሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል መነጋራቸውም ይታወሳል።
ኤርትራ፤ አሜሪካ በጦር መሪዋ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ "መሠረተ ቢስ" ስትል ውድቅ አደረገች
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል ከተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ ማእቀብ ይጣል በሚል የቀረበላቸውን የውሳኔ ሃሳብ በፊርማቸው ማጽደቃቸውም ይታወሳል፡፡
ማዕቀቡ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ መንግስት፣ በአማራ ክልል መስተዳደርና በህወሓት አመራሮች ላይ የሚያነጣጥር ነው መባሉም አይዘነጋም፡፡