የጸጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ የሶማሊያ ጉዳይ ላይ በዝግ መከረ
“ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሶማሊያ ሰላም፣ደህንነት እና መረጋጋት ቅድሚያ እንዲሰጡ”ም አሳስቧል “የሶማሊያን የግዛት አንድነት አከብራለሁ” ያለው ምክር ቤቱ
ምክር ቤቱ በምክሩ “በሶማሊያ የፖለቲካ አለመግባባት” ላይ ስጋት አለኝ አለ
የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታን በማስመከት ለሁለት ቀናት በዝግ መክሯል፡፡
ምክር ቤቱ ባደረገው ምክክር በሶማሊያ የተመድ ዋና ጸሃፊው ተወካይ ጀምስ ስዋን ያቀረቡትን ሪፖርት ካዳመጠ በኋላም መግለጫ አውጥቷል፡፡
በዚህም የፀጥታው ምክር ቤት “በሶማሊያ የፖለቲካ አለመግባባት” ላይ ስጋት እንዳለው ግልጽ አድርጓል፡፡
ምክር ቤቱ ስጋቱን የገለጸው በሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ (ፋርማጆ) እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሁሴን ሮብልን መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ቀጣዩን የምርጫ ሂደት ሊያስተጓጉል ይችላል ከሚል ነው፡፡
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የሃገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ገደቡ
የጸጥታው ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ “ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሶማሊያ ሰላም፣ደህንነት እና መረጋጋት ቅድሚያ እንዲሰጡ” ሲል አሳስቧል፡፡
እንደፈረንጆቹ መስከረም 17/2020 እና ግንቦት 27/2021 በተደረሱ ስምምነቶች መሰረት በሶማሊያ ለሚደረገው ሰላማዊና አሳታፊ የሆነ ምርጫ ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም አካላት ያሉዋቸው ልዩነቶች በውይይት ሊፈቱ ይገባልም ብሏል መግለጫው፡፡
ምክር ቤቱ የሶማሊያ ፌደራል መንግስትም ሆነ የፌደሬሽኑ ራስ ገዝ መንግስታት ማንኛቸውም የፖለቲካ ልዩነቶች “በጸረ-አልሻባብ እና ሌሎች ታጣቂ ኃይይሎች ትግላቸው ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ እንዳይኖር ማረጋጋጥ አለባቸው”ም ነው ያለው፡፡
በሶማሊያ ልአላዊነት፣የፖለቲካ ነጻነት፣ የግዛት አንድነት እና አንድነት እንደሚያከብርም ምክር ቤቱ ግልጽ ማድረጉም ሽንዋ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ (ፋርማጆ) እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሁሴን ሮብል ከቅርብ ጊዜት ወዲህ በከፋ ቅራኔ ውስጥ ነው የሚገኙት፡፡
የሶማሊያው ጠ/ሚ ሞሀመድ ሁሴን የሶማሊያ ብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተርን ከስራ አባረሩ
በተለይም የሃገሪቱ ደህንነት ባልደረባ የነበረችው ኢክራም ታህሊል ደብዛ መጥፋት ጋር በተያያዘ ሮብል የሃገሪቱን የደህነት ሹም ፋሃድ ያሲን ሀጂ ጣሂርን ከሃላፊነት አንስተው ይበልጥ አቃቅሯቸዋል፡፡
ፋርማጆ ፋሃድ ያሲን ሀጂ ጣሂርን ከስልጣን መነሳት በመቃወም የብሔራዊ ደህንነት አማካሪያቸው አድርገውም ሾመዋቸዋል፡፡
ሮብል በመንግስት ወጪዎች ላይ ያለ እሳቸው እውቅና የሚፈጸሙ ነገሮች እንዳይኖሩ በመስታወቅ እገዳ ጥለው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህ ቅራኔያቸው ተባብሶም ፋርማጆ በተራቸው “ሮብል ከስልጣኑ እያለፈ ነው” በማለት በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ሰልጣን ላይ ከቀናት በፊት እግዳ መጣለቸው የሚታወስ ነው፡፡