ብራዚል በሀገሯ ያለው የቢዋዲ መኪና ፋብሪካን ዘጋች
ሀገሪቱ ፋብሪካውን የዘጋችው ኩባያው የባሪያ ንግድ በሚመስል መልኩ የጉልበት ብዝበዛ ፈጽሟል በሚል ነው
መሰረቱን ቻይና ደረገው የመኪና አምራች ቢዋይዲ ከእስያ ውጪ የመጀመሪያውን ፋብሪካ በብራዚል ከፍቶ ነበር
ብራዚል በሀገሯ ያለው የቢዋዲ መኪና ፋብሪካን ዘጋች፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ኩባንያ የሆነው ቢዋይዲ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ፋብሪካውን በብራዚል ከፍቶ ነበር፡፡
ኩባንያው በብራዚሏ ካማካሪ በተሰኘችው ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ፋብሪካውን በውጭ ሀገር የከፈተ ሲሆን የፊታችን መጋቢት ወር ላይ ምርቱን ወደ ገበያ እንደሚያቀርብ ገልጾ ነበር፡፡
160 ሰራተኞች አሉት የተባለው ይህ የብራዚል ቢዋዲ ፋብሪካ በሰራተኞች ላይ የተጋነነ ጉልበት ብዝበዛ፣ እረፍት መከልከል፣ ደህንነቱ ባልተጠበቀ ስፍራ ማሰራት እና ማቆየት፣ ክፍያ በወቅቱ አለመክፈል ጉዳቶችን አድርሷል ተብሏል፡፡
ሰራተኞቹ እንዳይንቀሳቀሱ በሚል ፓስፖርታቸውን ሳይቀር ቀምቶ ነበር የተባለ ሲሆን የብራዚል ህግ አስከባሪዎች ፋብሪካውን ዘግተዋል፡፡
ቢዋይዲ በበኩሉ በብራዚል አለው ከተባለው ፋብሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዳቋረጠ ነገር ግን የሀገሪቱ ህግ አስከባሪ ተቋማት ውሳኔን እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡
የቻይናው ቢዋይዲ ኩባንያ ፎርድ እና ሆንዳን በመብለጥ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ተባለ
ቢዋይዲ ኩባንያ አሁን ላይ በዓለማችን ካሉ ቀዳሚ የመኪና አምራች እና ሻጭ ኩባንያ ሲሆን በ2025 ስድስት ሚሊዮን መኪኖችን ለመሸጥ ማቀዱን አስታውቋል፡፡
ቻይና የመኪና አምራች ኩባንያዎቿ በዓለም ገበያ እንዲወዳደሩ በሚል የተለያዩ ማበረታቻዎችን በማድረግ ላይ ስትሆን አሜሪካ እና አውሮፓ ደግሞ በቻይና ኩባንያዎች ላይ ማዕቀቦችን እየጣሉ ናቸው፡፡
ሀገራቱ ማዕቀቡን የሚጥሉት ኩባያዎቻቸውን ከኪሳራ ለማትረፍ እንደሆነ ተገልጿል፡፡