በቅርቡ ኢንተርኔት ያገኙት የብራዚል ጫካ ወንዶች አደን እያቆሙ ነው ተባለ
ወንዶች ለእለት ምግብ ፍጆታ አደን ማደን ቢኖርባቸውም ጊዜያቸውን የወሲብ ምስሎችን በማየት እያሳለፉ እንደሆነ ተገልጿል
ማሩቦ የሚባሉት የብራዚል ጎሳዎች ከስልጣኔ ተገለው ኑሯቸውን በጫካ አድርገዋል
በቅርቡ ኢንተርኔት ያገኙት የብራዚል ጫካ ወንዶች አደን እያቆሙ ነው ተባለ፡፡
ማሩቦ የተሰኘው የብራዚል ጎሳ 2 ሺህ አባላት ያሉት ሲሆን ላለፉት 100 ሺህ ዓመታት ኑሯቸውን በጫካዎች ውስጥ ያደረጉ ናቸው፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት በአሜሪካዊው ቢሊየነር ኢለን መስክ ንብረት በሆነው ስፔስ ኤክስ ኩባንያ እና በሌሎች በጎ ፈቃደኞች ድጋፍ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘት ችለዋል፡፡
እነዚህ የጫካ ነዋሪዎች ከኢንተርኔት ጋር በመገናኘታቸው ደስተኞች ሆነዋል ቢባልም ወጣቶች እና ወንዶች በኢንተርኔት ላይ ተጥደው ጊዜያቸውን እያሳለፉ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ኒዮርክ ታየምስ ዘገባ ከሆነ የማሩቦ ጎሳ ነዋሪዎች በኢንተርኔት አማካኝነት ከዓለም ጋር የተሳሰሩ መሆናቸው ደስታን ሰጥቷቸዋል፡፡
ይሁንና አደን በማደን ቤተሰቦቻቸውን በመመገብ ይታወቁ የነበሩ የጎሳው አባላት አሁን ላይ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ጊዜያቸውን እያባከኑ ነው ተብሏል፡፡
አብዛኛው የጎሳው አባላት በተለይም ወጣቶች እና ወንዶች የወሲብ ምስሎችን ሲያዩ እንደሚውሉ የተገለጸ ሲሆን ለሌሎች የበይነ መረብ ጥቃቶች እና ስርቆቶች እየደረሰባቸው እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ኢኖኩ ማሩቦ የተሰኘው የ40 ዓመት የዚህ ጎሳ አባላት ለዘመናት ከስልጣኔ ተገለው ይኖሩ እንደ ነበር ተናግሮ ኢንተርኔቱ ጥሩ እድል ቢሆንም በጫካ ውስጥ አደን ካላደንክ ህይወት አይቀጥልም ብሏል፡፡
የወሲብ ፊልሞችን ሲያዩ የሚውሉ የጎሳው አባላትም ከዚህ በፊት ታይተው የማይታወቁ የጾታ ጥቃቶችን እያደረሱ፣ በአደባባዮች ላይ መሳሳም እና ሌሎች ያልተገቡ ድርጊቶችን ለማድረግ እየሞከሩ እንደሆነም ተናግሯል፡፡
ይህ መሆኑ የማሩቦ ጎሳ የመጥፋት አደጋን ጨምሮ መገለሎች እና ሌሎች የስነ ልቦና ጥቃቶች በጎሳው አባላት ላይ ሊደርስባቸው ይችላልም ተብሏል፡፡
በማሩቦ ጎሳ አባላት ውስጥ በእድሜ ትልቋ የሆነችው የ73 ዓመቱ ጻይናማ ማሩቦ በበኩሏ ህይወት በዚህ አስቸጋሪ ሆኗል፣ ስንፍና በርትቷል የጎሳው አባላት ሁሉ የነጮችን ህይወት ለመሞከር ነው የሚጥሩት ሱሉ ተናግረዋል፡፡
እያንዳንዳቸው የማሩባ ጎሳ አባላት የአባታቸው ስም በጎሳው ማሩቦ የሚጠራ ሲሆን በብራዚል አማዞን ጫካ ኢቱዌ ወንዝን ተከትለው በአደን የሚተዳደሩ ህዝቦች ናቸው፡፡