ብራዚል በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደች
ኒኮላስ ኦተመንዲ በጭንቅላቱ ገጭቶ ባስገባት ግብ አርጀንቲና ብራዚልን 1-0 ማሸነፍ ችላለች
ብራዚል በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳዋ እና ለሶስተኛ ጊዜ በተከታታይ ሸንፈት አስተናግዳለች
ብራዚል በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደች።
በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር፣ ብራዚል የኳታሩን የአለም ዋንጫ ባነሳችው አርጀንቲና አሳዛኝ የሚባል ሽንፈት ደርሶባታል።
በፖሊስ እና በደጋፊዎች ግጭት ምክንያት ከተያዘለት መርሃግብር በግማሽ ሰአት በዘገየው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኒኮላስ ኦተመንዲ በጭንቅላቱ ገጭቶ ባስገባት ግብ አርጀንቲና ብራዚልን 1-0 ማሸነፍ ችላለች።
በአለም እጅግ ስኬታማ በሆኑት ቡድኖች መካከል ያለው ተቀናቃኝነት የተባባሰው የብራዚል ፖሊስ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘመር ረብሻችኋል በሚል ምክንያት የአርጀንቲና ደጋፊዎችን መምታቱን ተከትሎ ነበር።
በሊዮነል ሚሴ የሚመሩት የአለም ዋንጫ አሸናፊ ተጨዋቾች ወደ አደባባይ በመውጣት ሁኔታው እንዲረጋጋ ጥረት አድርገዋል ተብሏል።
በስቴዲየሙ ውስጥ የአምስት ጊዜ የአለም ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ብራዚል ያልተለመደ ተከታታይ የማጣሪያ ጨዋታ ሽንፈት ያበሳጫቸው ደጋፊዎች ከፍተኛ ጩኸት አሰምተዋል።
ይህም ሆኖ ብራዚል በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳዋ እና ለሶስተኛ ጊዜ በተከታታይ ሸንፈት አስተናግዳለች።
ከጅምሩ በርካታ ችግሮች የተስተዋሉበት ይህ ጨዋታ 22 ካርዶች የተመዘዙበት፣ በሜዳ ላይ በርካታ ግጭቶች የተፈጠሩበት እንዲሁም የተቀናቃኝ ቡድኖች ደጋፊዎች በተደጋጋሚ የተጋጩበት ነበር።
በዚህ ጨዋታ ብራዚል ቪንሺየስ ጁኒየርን እና ኔይማርን በጉዳት ምክንያት ማሰለፍ ሳትችል ቀርታለች።
ብራዚል ከአርጀንቲና በስምንት ነጥብ ዝቅ ብላ ተገኛለች።