የ2026ን የአለም ዋንጫ አሜሪካ፣ ካናዳና እና ሜክሲኮ በጋራ እንዲያዘጋጁት ፊፋ ውስኗል
ኤርትራ ከአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ራሷን አገለለች።
ኤርትራ ከሞሮኮ ጋር ልታደርገው የነበረው የመጀመሪያ ጨዋታ ቀናት ሲቀሩት ከ2026ቱ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ራሷን ማግለሏን ፊፋ አስታውቋል።
ኤርትራ ለምን ከውድድሩ እንደወጣች ምክንያቷን ግለጽ አላደረገችም ተብሏል።
በቡድን 'ኢ' የተደለደለው የኤርትራ ቡድን ወደሞሮኮ እንዲጓዝ መርሃግር ውጥቶ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።
"ፊፋ እና ካፍ የኤርትራ ብሔራዊ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ውድድር ራሱን ማግለሉን ማረጋገጥ ችለዋል" ሲል ፊፋ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ፊፋ ሁሉም የኤርትራ ጨዋታዎች ተሰርዝዋል ብሏል። የቀሪዎቹ ቡድን 'ኢ' አባላት ጨዋታ መርሃግብር አለመቀየሩንም ፊፋ ገልጿል።
የ2026ን የአለም ዋንጫ አሜሪካ፣ ካናዳና እና ሜክሲኮ በጋራ እንዲያዘጋጁት ፊፋ ውስኗል።
ፊፋ በዚህ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የተሳታፊ ሀገራትን ብዛት ከ32 ወደ 48 ከፍ እንዲሉ አድርጓል። ጨዋታው በሶስት ሀገራት እንዲካሄድ በፊፋ የተላለፈው ውሳኔ የውድድሩን ድባብ ያደበዝዘዋል የሚል ቅሬታ ቀርቦበታል።
የ2022ቱን የኳታር ዓለም ዋንጫ ደቡብ አሜካዊቷ አርጀንቲና ፈረንሳይን በማሸነፍ ዋንጫ ማንሳቷ ይታወሳል።