ኑኔዝ በ42ኛው ደቂቃ በብራዚል ላይ ግብ በማስቆጠሩ በኔይማር መውደቅ ያዘነውን የብራዚል ምሽት የበለጠ አደብዝዞታል
ብራዚል በኡራጓይ 2-0 በተሸነፈችበት ጨዋታ ኔይማር ጁኔር ጉዳት አስተናግዷል።
ብራዚል እና ኡራጓይ ባካሄዱት የ2026 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር፣ ኡራጓይ በዳርዊን ኑኔዝ እና በኒኮላስ ዲ ላ ክሩዝ ሁለት ግቦች አሸንፋለች። በዚህ ጨዋታ ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ተረከዙ ላይ በደረሰበት ከባድ ጉዳት የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሊያበቃ ሲል ከሜዳ መውጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኑኔዝ በ42ኛው ደቂቃ በብራዚል ላይ ግብ በማስቆጠሩ በኔይማር መውደቅ ያዘነውን የብራዚል ምሽት የበለጠ አደብዝዞታል።
ኔይማር ለበርካታ ደቂቃዎች ሜዳ ላይ ህክምና ከተደረገለት በኋላ በስትሬቸር ወጥቷል።
የብራዚል እግርኳስ ፌደሬሽን ምንጮች እንደገለጹት ኔይማር በግራ ተረከዙ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባት እና የጅማት ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ ለማረጋገጥ ምርምራ ይደረግለታል።
ዲ ላ ክሩዝ በ77ኛው ደቂቃ ላይ ኑኔዝ ያቀበለውን ኳስ ወደ ግብ በመቀየር አስተናጓጇ ኡራጋይ እንድትመራ አድርጓታል።
ኡራጓይ ያገኘችው ድል ሰባት ነጥብ በመያዝ ደረጃዋን እንድታሻሽል አስችሏታል።