የጎርፍ ተጎጂዎችን ለመርዳት የኦሎምፒክ ህልማቸውን ያጨናገፉ የብራዚል አትሌቶች
የብራዚል ኦሎምፒክ ኮሚቴ አትሌቶቹን ወደ ሌላ የብራዚል ክፍል ለመውስድ ቢያቅድም፣ አትሌቶቹ ከሪዮ ግራንዴ ዱ ሶል መውጣት አልፈለጉም
የፓሪስ የሚካሄደው ኦሎምፒክ ውድድር ከሶስት ወራት ያልበለጠ ጋዜ ሲቀረው፣ የብራዚል አትሌቶች ውድድሩን ሰርዘው ተጎጅዎችን በመፈለግ እየተሳተፉ ናቸው
በፈንሳይ ፓሪስ የሚካሄደው ኦሎምፒክ ውድድር ከሶስት ወራት ያልበለጠ ጊዜ ሲቀረው፣ በጎርፍ በተጎዳችው ሪዮ ግራንዴ በተባለችው ግዛት የሚገኙ የብራዚል አትሌቶች ውድድሩን ሰርዘው ተጎጂዎችን በመርዳት እየተሳተፉ ናቸው።
በቀላል ክብደት የጀልባ ቀዘፋ ዘርፍ ሊወዳደሩ የነበሩት ሮውረስ ኢቫልዶ ቤከር እና ፔድሮ ቱችቴንሀገን የስፓርት ህልማቸውን በመተው በጎርፉ ምክንያት መውጫ ያጡ ሰዎችን የሚያድኑትን፣ መጠለያ የሚያዘጋጁትን እና እርዳታ የሚያከፋፍሉትን በጎ ፈቃደኞች ተቀላቅለዋል።
"ለፔድሮ ከዚህ በኋላ አልወዳደርም አልኩት" ይላል ቤከር።
"ኦሎምፒክ ህልማችን ነበር፤ ነገርግን አሁን ላይ ከዚህ መሄድ አንችልም" ሲል ቱችቴንሀገን ተናግሯል።
የጉቢያ ወንዝ ሞልቶ የግዛቷን ዋና ከተማ ፓርቶ አልጀሬ ዋና መንገዶች በማጥለቅለቁ ምክንያት ስልጠናቸውም ተስተጓጎለ። በዚህ ምከንያት አትሌቶቹም እርዳታ ወደማከፋፈል እና ሰዎችን መርዳት ሊጀምሩ ችለዋል።
"ሁለት ጊዜ አላስብም ነበር። በኦሎምፒክ ለመሳተፍ ይህ የመጨረሻ እድሌ ነበር። ደስተኛም ነበርኩ። ነገረግን ዛሬ ጎርፉ የሰው ህይወት እንቀጠፈው ሁሉ የእኔንም ህልም አበላሽቷል" ብሏል ቤከር።
የዓለም እና የኦሎምፒክ ሰርፊንግ አሸናፊው ኢታሎ ፌረራ የነፍስ አድን ስራውን ለማገዝ ወደ ሪዮ ግራንዴ ዱ ሶል አቅንቷል። የብራዚል የወንዶች ጁዶ ቡድን አስልጣኝ የሆነው አንቶኒዮ ካርሎስ ካኮ ፔሬራም የነፍስ አድን ዘመቻውን ተቀላቅሏል።
የብራዚል ኦሎምፒክ ኮሚቴ አትሌቶቹን ወደ ሌላ የብራዚል ክፍል ለመውስድ ቢያቅድም፣ አትሌቶቹ ከሪዮ ግራንዴ ዱ ሶል መውጣት አልፈለጉም።
300 ሺ ሰዎችን ከቤታቸው ያፈናቀለው በሪዮ ግራንዴ ሱል የተከሰተው ያልተጠበቀ ጎርፍ 113 ሰዎች ህይወታቸው እንዲልፍ እና 146 ሰዎች ደግሞ እንዲጠፉ ምክንያት መሆኑን የሀገሪቱ ሲቪል ዲፌንስ ገልጿል።