የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትረስ ከስልጣናቸው ሊነሱ እንደሚችሉ ተገለጸ
ከ100 በላይ የሀገሪቱ ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚንስትር ትሩስ ድጋፍ እንደማይሰጡ ተገልጿል
በብሪታንያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ሶስት ጠቅላይ ሚንስትሮች ስልጣን ለቀዋል
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትሩስ ከስልጣናቸው ሊነሱ እንደሚችሉ ተገለጸ።
ብሪታንያ ከመሰረተችው እና አባል ከሆነችበት የአውሮፓ ህብረትን በህዝበ ውሳኔ ከለቀቀችበት ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ ትገኛለች።
ዓለመረጋጋቱን ተከትሎም ሶስት ጠቅላይ ሚንስትሮች ስልጣናቸውን በጫና ምክንያቶች ለቀዋል።
ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በምክር ቤቱ አባላት ጫና ምክንያት ስልጣን ለመልቀቅ መገደዳቸው ይታወሳል።
ይሄንን ተከትሎም ከ45 ቀናት በፊት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትሩስ ስልጣን እንዲለቁ ግፊት እየተደረገባቸው እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
የብሪታንያ የወቅቱ ገዢ ፓርቲ የሆነው የወግ አጥባቂ ፓርቲን ወክለውን በሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት ውስጥ ያሉ ተመራጮች ጠቅላይ ሚንስትር ትሩስ ድጋፍ እንደማይሰጡ በመናገር ላይ ናቸው ተብሏል።
ከ100 በላይ የዚህ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚንስትር ትሩስ የመተማመኛ ምርጫ እንዲካሄድ በመወትወት ላይ እንደሆኑ ዘገባው ጠቅሷል።
የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩስን መቃወም የጀመሩት ባሳለፍነው ሳምንት የብሪታንያ ግምጃ ቤት ተጠሪ ሆነው የተሾሙት ጀርሚ ሀንት የኢኮኖሚ ስትራቴጂ የላቸውም በሚል ነው።
እንደ ዘገባው ከሆነ የተወሰኑ የምክር ቤት አባላት በድብቅ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሾም ውይይት ጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትሩስ የዋጋ ግሽበቱን ተከትሎ እየወሰዱት ባለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክንያት ጫና ውስጥ መግባታቸው ይገለጿል።