ግለሰቦቹ የሰረቁትን ገንዘብ እንዲመልሱ ቢጠየቁም መካዳቸውን ተከትሎ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል
በ12 ሰከንድ ውስጥ 25 ሚሊዮን ዶላር የሰረቁት ወንድማማቾች
አንተን ፔራሬ እና ጀምስ ፔራሬ የተሰኙት በአሜሪካዊያን የዓለማችን ምርጥ ተብሎ ከሚጠራው ዩንቨርሲቲ ማሳቹሴትስ ዩንቨርሲቲ በሒሳብ እና ኮምፒውተር ሳይንስ ተመርቀዋል፡፡
የ24 እና 28 ዓመት እድሜ ያላቸው እነዚህ ወንድማማቾች በ12 ሰከንዶች ውስጥ 25 ሚሊዮን ዶላር መዝብረዋል ተብሏል፡፡
ወንድማማቾቹ እውቀታቸውን ተጠቅመው ኢቴሪየም የተባለ የክሪፕቶ ከረንሲ ድረገጽን ሰብረው በመግባት ገንዘቡን ወደ ራሳቸው አካውንት አዘዋውረዋል የተባለ ሲሆን ይህን ለማድረግ የፈጀባቸው ጊዜ 12 ሰከንዶች ብቻ ናቸው፡፡
ሰሜን ኮሪያ 1 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ክሪፕቶከረንሲ ዘርፋለች ሲል የመንግስታቱ ድርጅት ገለጸ
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ወንድማማቾቹ ገንዘቡን የሰረቁት ከአንድ ዓመት በፊት ሲሆን እንዲህ አይነት ስርቆት ሲፈጸም በታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የስርቆቱ መፈጸም በአሜሪካ ክሪፕቶ ከረንሲ ኢንዱስትሪ ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ የገለጸው የሀገሪቱ ፍትህ ቢሮ ወንድማማቾቹ ገንዘቡን እንዲመልሱ ቢጠየቁም እንዳልሰረቁ እና ገንዘቡ የራሳቸው መሆኑን ለማሳየት ጥረቶችን አድርገዋል ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ወንጀል መርማሪዎች እንዳሉት መሰል የስርቆት ወንጀል ሲፈጸም እና ክስ ሲመሰረት ህ የመጀመሪያው ነው ያሉ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡