ስፖርት
በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተሳተፉ 195 ሀገራት ሜዳሊያ ያገኙት 46ቱ ብቻ ናቸው
ውድድሩን በስድስተኛነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል
አሜሪካ ፣ ካናዳ እና ስፔን ውድድሩን ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያጠናቀቁ ሀገራት ናቸው
በቡዳፔስት ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድር ላይ ከተሳተፈ 195 ሀገራት ሜዳሊያ ያገኙ 46ቱ ብቻ ናቸው።
ከነሀሴ 13 ቀን እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ሲካድየ ቆየው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል።
በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 195 የዓለማችን ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን ሜዳሊያ ማግኘት የቻሉ ሀገራት ግን 46 ብቻ ናቸው ተብሏል።
ከማጣሪያ ውድድሮች ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ 2 ሺህ 100 አትሌቶች በተሳፉበት በዚህ ውድድር ላይ 50 አትሌቶች የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ሲያስገኙ 48 የብር እንዲሁም 50 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ተወዳዳሪዎቹ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡
ውድድሩን 400 ሺህ ተመልካቾች በአካል ስታዲየም ገብተው ታድመውታል የባለ ሲሆን ሀንጋሪ ደማቅ እና አይረሴ ውድድር ማዘጋጀቷ ተገልጿል።
በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀው ይህ ውድድር 52 አይነቶች የተካሄደ ሲሆን አሜሪካ በበላይነት አጠናቃለች።