ኢትዮጵያ ውድድሩን ከዓለም ስድስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች
በቡዳፔስት ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድር ላይ 195 መሳተፋቸ ተገ ለጸ።
ከነሀሴ 13 ቀን እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ሲካድየ ቆየው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል።
በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 195 የዓለማችን ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን ሜዳሊያ ማግኘት የቻሉ ሀገራት ግን 46 ብቻ ናቸው ተብሏል።
ከማጣሪያ ውድድሮች ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ 2 ሺህ 100 አትሌቶች በተሳፉበ ት በዚህ ውድድር ላይ 50 አትሌቶች የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ሲያስገኙ 48 የብር እንዲሁም 50 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ተወዳዳሪዎቹ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡
ውድድሩን 400 ሺህ ተመልካቾች በአካል ስታዲየም ገብተው ታድመውታል የባለ ሲሆን ሀንጋሪ ደማቅ እና አይረሴ ውድድር ማዘጋጀቷ ተገልጿል።
በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀው ይህ ውድድር52 አይነቶች የተካሄደ ሲሆን አሜሪካ በበላይነት አጠናቃለች።
አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ያላግባብ ከውድድር አለመቀነሱን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ
አሜሪካ በዚህ ውድድር ላይ 12 ወርቅ 8 ብር እና 9 ነሀስ በድምሩ 29 ሜዳሊያዎችን ሰብስባለች።
ውድድሩን በሜዳሊያ ብዛት በሁለተኝነት ያጠናቀቀችው ካናዳ በ4 ወርቅ በ2 ብር በድምሩ ስድስት ሜዳሊያዎችን ስትወስድ ስፔን ደግሞ በ4 ወርቅ እና በአንድ ብር በድምሩ በአምስት ሜዳሊያዎች ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።
የካሪቢያኗ ሀገር ጃማይካ በ3 ወርቅ፣ አምስት ብር እና አራት ነሀስ በምሩ በ12 ሜዳሊያዎች አራተኛ ስትሆን ጎረቤት ሀገር ኬንያ በ3 ወርቅ፣ ሶስት ብር እ ንዲሁም በአራት ነሀስ በድምሩ በ12 ሜዳሊያዎች ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪጫ ደኍ ሞ በአንደኝነት አጠናቃለች።
ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ፣ በአራት ብር እንዲሁም በሶስት ነሀስ ሜዳሊዎች በድምሩ በ9 ሜዳሊያዎች ከዓለም ስድስተኛ ከአፍሪካ ሁለተኛ ሆና ማጠናቀ ቋን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድረገጹ አስታውቋል።