ፕሬዝደንት ባይደን የልጃቸውን ጥፋተኛ መባል ተከትሎ ምን አሉ?
የባይደን ልጅ የጦር መሳሪያ ለመግዛት ሲል ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት በፍ/ቤት ጥፋተኛ ተባለ
ስልጣን ላይ ባለ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ልጅ ላይ በቀረበ የመጀመሪያ ክስ፣ ሀንተር ባይደን በቀረቡበት ሶስት ክሶች ጥፋተኛ ተብሏል
የባይደን ልጅ የጦር መሳሪያ ለመግዛት ሲል ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት በፍ/ቤት ጥፋተኛ ተባለ።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን ልጅ እፅ መጠቀሙን ከደበቀ በኋላ በህገወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ በመግዛት ጥፋተኛ ተብሏል።
በስልጣን ላይ በላ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ልጅ ላይ በተፈጸመ የመጀመሪያ ክስ፣ የ54 አመቱ ሀንተር ባይደን ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ በቀረቡበት ሶስት ክሶች ጥፋተኛ መባሉን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ሀንተር፣ ሪቮልቨር ሽጉጥ ለመግዛት በመንግስት የማጣሪያ ቅጽ ላይ የእፅ ሱስ እንደሌለበት የሚገልጽ ሀሰተኛ መረጃ መስጠትን እና ለ11 አመታት በህገወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ መያዝን ጨምሮ የቀረቡበትን ክሶች አልፈጸምኩም ሲል ተከራክሯል።
ችሎቱ ለሶሰት ሰአታት የቆየ ሲሆን የጥፋተኝነት ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ የደረሱት ቀዳሚዊት እመቤት ጁል ባይደን የእንጀራ ልጃቸውን እጅ ይዘው ሲወጡ ታይተዋል።
በልጃቸው ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ ፕሬዝደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ተናግረዋል።ዘንተር ግን በውሳኔው ላይ ይግባኝ ለማለት እየሰበ ነው።
የሀንተር የቀድሞ ሚስት እና እህቱ፣ ሀንተር መሳሪያ ከመግዛቱ በፊት እና በኋላ ከፍተኛ ሱስ ውስጥ ተዘፍቆ እንደነበር ፍርድ ቤት ቀርበው አስረድተዋል። አቃቤ ህግም መሳሪያ በሚገዛበት ወቅት ሱስ ውስጥ መሆኑን ያሳያሉ ያላቸውን የጹህፍ መልእክቶችን፣ ፎቶዎችን እና የባንክ አካውንቶችን አሳይተዋል።