የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የማስታወስ ችሎታየ አሪፍ ነው ሲሉ ለስፔሻል ካውንስሉ መልስ ሰጥተዋል
የሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የማስታወስ ችሎታየ አሪፍ ነው ሲሉ ለስፔሻል ካውንስሉ መልስ ሰጥተዋል።
ፕሬዝደንቱ ጥብቅ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በአግባቡ አልያዙም እንዲሁም ወሳኝ ሁነቶች ማስታወስ ተስኗቸዋል የሚለውን የምርመራ ውጤት አጣጥለውታል።
ባይደን በትናንትናው እለት በሰጡት ድንገተኛ መግለጫ "የማስታወስ ችሎታየ አሪፍ ነው" ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ልጃቸው የሞተበትን ቀን ማስታወስ አልቻሉም የሚለውንም የምርመራ ውጤት አይቀበሉትም።
መርማሪው ባይደን በ2017 ከምክትል ፕሬዝደንትነት ሲሰናበቱ ጥብቅ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ይዘው ወጥተዋል ብሏል።
ነገርግን መርማሪው ፕሬዝደንት ባይደንን እንደማይከሳቸው ገልጿል።
በፕሬዝደንት ባይደን ላይ ምርመራ ያካሄዱት የፍትህ ዲፖርትመንት ስፔሻል ካውንስል ሮበርት ሁር ባይደን ከምክትል ፕሬዝዳንትነት ስልጣን ከለቀቁ በኋላ በአፍጋኒስታን ከነበረው ጦርነት ጋር የተያያዙ ጥብቅ የወታደራዊ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መረጃዎች ይዘው ተገኝተዋል ብለዋል።
345 ገጽ ያለው የምርመራ ውጤት ፕሬዝደንቱ የማስታወስ ችሎታ ውስንነት እንዳለበት የሚያሳይ ነው።
ሁር በምርመራው ሂደት የ81 አመቱን ፕሬዝደንት አምስት ጊዜ ቃለመጠይቅ አድርገውላቸዋል።
ስፔሻል ካውንስሉ እንዳሉት ፕሬዝደንቱ ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑበትን ወቅት (2009-2017) እና ከበርካታ አመታት በፊት ልጃቸው ቢዩ የሞተበትን(2015) ማስታወስ አልቻሉም።
ፕሬዝደንት ባይደን በማስታወስ ችሎታቸው ላይ ጥያቄ የፈጠረውን የምርመራ ውጤት ስሜታዊ ሆነው አጣጥለውታል።
ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለምን እቤታቸው እንዳስቀመጡ ሲጠየቁ፣ ፕሬዝደንቱ ስራተኞቻቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ሰራተኞቻቸው ሚስጥራዊ መረጃዎችን ማስቀመጣቸውን እንደማያውቁ ተናግረዋል።