የተሽከርካሪዎች የመጫን አቅም ቢቀንስም የታሪፍ ጭማሪ አንደማይኖር ቢሮው አስታውቋል
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የህዝብ ትራስፖርት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን እንዲቀንሱ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
አዲሱ መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ቢሮው አስታውቋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አከለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በአዲሱ መመሪያ መሰረት ተሽከርካሪዎች የሚቀንሱበት መጠን ይለያያ አንጂ ሁሉም አይነት የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የተሳፋሪ ቁጥር ይቀንሳሉ ብለዋል፡፡
በኢዲሱ መመሪያ መሰረት ታክሲዎች በወንር ሙሉና እና ከኋላ ሶስት ሰውና ሃይገሮች (ቅጥቅጦች) በወንበር ልክና ተራርቀው የሚቆሙ 5 ሰዎች እንዲጭኑ ያዛል ብለዋል ኃላፊው፡፡
መመሪያው ባሶች ደግሞ በሙሉ ወንበርና ተጨማሪ ከሚጭኑት በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ እንደሚገደረግ ተገልጿል፡፡
የተሽካርካሪዎች የመጫን አቅም ዝግ ቢልም በታሪፍ ላይ የተለየ ጭማሪ አይኖርም ብሏል ቢሮው፡፡ የመመሪያውን ተፈጻሚነት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ቢሮ ይቆጣጠራሉ ተብሏል፡፡
ይህን መመሪያ ተላልፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ከ500 እስከ 5ሺ የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከመጋቢት ጀምሮ እስከ ነሀሴ 2012 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ወራት የቆየ በአዋጁ መሰረት ታክሲዎች በግማሽ እንዲጭኑ ሲደረግ፣ታክሲዎች በግማሽ እንዲጭኑ ተሳፋሪዎች የመጀመኛውን ታሪፍ እጥፍ ሲከፍሉ ነበር፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃ መቆየቱ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ካሉ አጠቃላይ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 62 በመቶ ያህሉ በአዲስ አበባ እነደሚገኙ ከፌደራል ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ጀረጃ መጨመሩንና የጽኑ ህሙማን ክፍልም እንዳለቀ የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡