ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ባለፈው አመት የትራንስፖርት ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ገደቦች ተጥለው ነበር
የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።
የቢሮው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ለመቀነስ የትራንስፖርት ቢሮ አዲስ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ከዚህ በፊት የተሽከርካሪዎችን የመጫን አቅም መወሰን፤ የታሪፍ መጠን ላይ ማሻሻያ ማድረግ፤ አውቶሞቢሎን በሙሉ እና በጎዶሎ ቁጥር ማሰማራት እና ሌሎች ስራዎች በቢሮው መመሪያዎች ተዘጋጅተው ሲተገበሩ ቆይተዋል።
ይሁንና የቫይረሱ ስርጭት አሁን ላይ እየጨመረ በመምጣቱ አዲስ የትራንስፖረት መመሪያ መዘጋጀቱን አቶ አረጋዊ ተናግረዋል።
የመመሪያው ሙሉ ይዘት በነገው ዕለት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አቶ አረጋዊ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከመጋቢት ጀምሮ እስከ ነሀሴ 2012 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ወራት የቆየ በአዋጁ መሰረት ታክሲዎች በግማሽ እንዲጭኑ ሲደረግ፣ታክሲዎች በግማሽ እንዲጭኑ ተሳፋሪዎች የመጀመኛውን ታሪፍ እጥፍ ሲከፍሉ ነበር፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃ መቆየቱ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ካሉ አጠቃላይ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 62 በመቶ ያህሉ በአዲስ አበባ እነደሚገኙ ከፌደራል ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።