ትራንስፖርት ቢሮው አዲስ የስምሪት ውሳኔውን እንዲቀር ማድረጉን ገለጸ
እቅዱ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት እስከሚደረግበት ድረስ የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ባለበት ይቀጥላል ብሏል ቢሮው
ቢሮው ከትምህርት መከፈት ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ መጨናነቆችን ለመቀነስ የተወሰኑ የከተማዋ መስመሮች ለብዙሀን ትራንስፖርት አግልግሎት ብቻ ክፍት እንዲሆኑ ወስኖ ነበር
ትራንስፖርት ቢሮው አዲስ የስምሪት ውሳኔን እንዲቀር ማድረጉን ገለጸ።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከትምህርት መከፈት ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ የትራፊክ መጨናነቆችን ለመቀነስ የተወሰኑ የከተማዋ መስመሮች ለብዙሀን ትራንስፖርት አግልግሎት ብቻ ክፍት እንዲሆኑ ወስኖ ነበር።
ቢሮው አሁን ከመሸ ባወጣው መግለጫ ይህን ውሳኔውን እንዲቀር አድርጎታል።
እቅዱ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት እስከሚደረግበት ድረስ የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ባለበት ይቀጥላል ብሏል ቢሮው።
ትራንስፖርት ቢሮው ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ 14 መስመሮችን ይፋ አድርጎ ነበር።
ለብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ተለይተው የነበሩት መስመሮች ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ አውቶቢስ ተራ፣ ከቦሌ- ሽሮሜዳ፣ ከጀሞ- ፒያሳ እና ከጀሞ- ሜክሲኮ፣ ከፒያሳ- ቦሌ፣ ከሜክሲኮ- ቦሌ፣ ከአራት ኪሎ- ቦሌ፣ ከአውቶቡስ ተራ- ቦሌ፣ ከሽሮ ሜዳ- ቦሌ፣ ከፒያሳ ጀሞ እና ከሜክሲኮ - ጀሞ ነበሩ።
የብዙሃን ትራንስፖርት ከ8 ሰው በላይ መያዝ የሚችሉ ተሽከርካሪዎችን የሚያጠቃልል ነው።