![](https://cdn.al-ain.com/images/2019/12/04/223-191411-fifa_15de7cd43d80a8_700x400.jpg)
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአለም እና የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት የስራ ሀላፊዎችን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ ህዳር 24/2012 ዓ.ም. ነው ሀላፊዎቹን በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ተቀብለው ያነጋገሩት፡፡
ውይይቱም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ግንቦት በምታስተናግደው የአለም እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ጉባኤ ላይ ያተኮረ ነበር የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው ፡፡
ኢትዮጵያ በቀጣዩ ግንቦት ወር የሚካሄደውን የዓለም እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ጉባኤ ታስተናግዳለች።
ጉባኤው ዘንድሮ ለሰባኛ ጊዜ የሚካሄድ ነው፡፡