ሊቢያ አለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳታካሂድ ለ10 አመት ተጥሎባት የነበረው እግድ ተነሳላት
በሊቢያ በትሪፖሊና በቤንጋዚ በሚገኙ ስቴዲየሞች ላይ በተደረገ የጥንቃቄና የደህንነት ፍተሻ አለምአቀፍ ውድድሮችን እንድታካሂድ ኮንፌደሬሽን ኦፍ አፍሪካን ፉትቦል (ካፍ) መፍቀዱን አስታውቋል፡፡
ካፍ ባወጣው መግለጫ የካፍ የአስቸኳይ ኮሚቴ ሊቢያ አለምአቀፍ የእግርካስ ውድድሮችን እንዳታካሂድ ጥሎባት የነበረውን እግድ አንስቷል፡፡
የእግርኳስ ውድድሮች አሁን ወደ ሊቢያ መመለሳቸውንና በቤንጋዚ ስቴድየም መጀመሩን የገለጸው መግጫው ውድድር ለማካሄድ ግን ብዙ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሷል፡፡
የካፍ ማረጋገጫ የወጣው የሊቢያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት አብዱል ሀኪም አል ሻልማኒ አለምአቀፍ ጨዋታዎች እንዳይካሄዱ ለ10 አመት ተጥሎ የነበረውን እግድ መነሳቱን ከሳወቁ በኋላ ነው፡፡ በፈረንጆቹ 2011 የሊቢያው መሪ መአማር ሃ ጋዳፊ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በተከሰተው የእርስበእርስ ጦርነት ምክንያት ነበር አለምአቀፍ ውድድር እንዳይካሄድ ማእቀብ የተጣለው፡፡
እግዱ የሊቢያ ክለቦችና ብሄራዊ ቡድን ውድድራቸውን በጎረቤት ሀገራት ማለትም በግብጽ፣በማሊ፣በመሮኮና በቱኒዚያ እዲያካሂዱ አስገድዷቸው ቆይቷል፡፡ ምንምእንኳን ማእቀቡ በፈረንጆቹ 2013 ለተወሰነ ጊዜ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም እንደገና እገዳው መጣሉ ይታወሳል፡፡
ካፍ ሊቢያ የካፍን የክለብ ፍቃድ፣የጥንቃቄና የጸጥታ መመዘኛዎችን እንድታሟላ እስከ ፈረንጆቹ የካቲት 10 ድረስ ቀነ ገደብ አስቀምጧል፡፡