በተመድ እውቅና ያለው የሊቢያ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፈው መስከረም ወር ነበር
በተመድ እውቅና ያለው የሊቢያ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፈው መስከረም ወር ነበር
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዕውቅና ያለው የሊቢያ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑትን ውሳኔ መሻራቸውን ቃል አቀባያቸው አስታወቁ፡፡
የመንግስት ቃል አቀባይ ጋሊብ አል ዛክላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ የሊቢያ የፖለቲካ ውይይት አልባት አግኝቶ እስኪጠናቀቅ በሥራቸው ላይ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ይህ ውሳኔ የመጣው የሀገሪቱ ከፍተኛ ምክር ቤት አዲስ ፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት እስኪመረጥ የሥልጣን ክፍተት እንዳይፈጠር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃላፊነት እንዲቆዩ ከተወሰነ በኋላ ነው ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን የቀለበሱት ተብሏል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ በኃላፊነት መቆየት በሀገሪቱ የሥልጣን ክፍተት እንዳይፈጠር ከማድረግም አንጻር ለትሪፖሊ መረጋጋት ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ ለሊቢያ እና በትሪፖሊ ያለው ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒሰትር ፋይዝ አልሳራጅ ውሳኔያቸውን እንዲቀለብሱ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ዕውቅና ያለው የሊቢያ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፈው መስከረም ወር እንደነበር ይታወሳል፡፡ እርሳቸውን የሚተካ አዲስ የሥራ ኃላፊ እንዲሾምና ይህም ጥቅምት ላይ ይፈጸማል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ሊቢያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዕውቅና ባለው የጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ መንግስትና በጀነራል ካሊፋ ሃፍታር በሚመራው የሊቢያ ብሔራዊ ጦር እሰጥ አገባ ስትናጥ ቆይታለች፡፡ ከቀናት በፊት ግን የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡