አምስት ሰዎች በአሳ አጥማጆች አማካኝነት ከመስጠም መዳናቸውን አይ ኦኤም አስታውቋል
አምስት ሰዎች በአሳ አጥማጆች አማካኝነት ከመስጠም መዳናቸውን አይ ኦኤም አስታውቋል
አለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው በሊቢያ ምእራባዊ ጫፍ ስደተኞችን አሳፍራ የነበረችው መርከብ በመሰበሯ ምክንያት በትንሹ 15 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
አይ ኦኤም እንደገለጸው አምስት ሰዎች በአሳ አጥማጆች አማካኝነት ከመስጠም ድነዋል፡፡
ከ200 በላይ የሚሆኑ ህገወጥ ስደተኞች መሞታቸውንና ሌሎች 280 የሚሆኑ ሰዎች በሜዲትራኒያን ባህር ሲጓዙ ደብዛቸው መጥፋቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በዚህ አመት ወደ 10ሺ የሚጠጉ ስደተኞች በሊቢያ ባህር ከመስጠም መዳናቸውንና ባለፈው አመት ደግሞ 9225 ሰዎች መዳናቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡
ሊቢያን 4 አስርት አመታት ያህል የገዙት ሟቹ ሙአማር ጋዳፊ በ2011 ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ፣ ሊቢያ ወደ አዉሮፓ ለመድረስ ተስፋ ለሚያደርጉ ስደተኞች ተመራጭ ቦታ ሆናለች፡፡
አይኦኤም በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሊቢያ ለስደተኞች ተመራጭ ቦታ አይደለችም፤ ምክንያቱም የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቷል፡፡