ፖለቲካ
የሲሪላንካ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ለመልቀቅ ከተስማሙ በኋላ መረጋጋት ሰፍኗል
ተቃውሞው የተነሳው በሀገሪቱ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ ነበር
ተቃዋሚዎች በትናንትናው እለት ቤተመንግስት በመግባት የፕሬዝዳንቱን ቤት ሰብረው ገብተዋል
የሲሪላንካ ፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፖክሳ ስልጣን ለመልቀቅ ከተስማሙ በኋላ የሀገሪቱ የንግድ ከተማ ኮሎምቦ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች፤ተቃዋሚዎቹም ደስተኛ ሆነዋል።
በሀገሪቱ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ፣ተቃውሟቸውን ለማሰማት የተሰባሸቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ቤተመንግስት በመግባት የፕሬዝዳንቱን ቤት ሰብረው ገብተዋል።
በትናንትናው እለት የሲሪላንካን ሰንደቅ አላማ የሚያውለበልቡ ተቃዋሚዎች በቅኝ ግዛት ዘመን የተሰራውን የፕሬዝደንቱን መኖሪያ ቤት በማጥለቅለቅ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ዘለው ገብዋል፤ አልጋ ላይም ተቀምጠዋል።
ሌሎች ደግሞ ስልጣን እንደሚለቁ ወደ ተስማሙት ጠቅላይ ሚኒሰትር ራኒል ዊከር መሽንጌ ቤት በመሄድ ያሻቸውን አድርገዋል።
የፖርለማው ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት ራጃፖክሳ ለሩብ ምእተ አመት ያህል ከታሚል አማጺያን ጋር የነበረውን ጦርነት አሸንፈዋል።
ለወራት የቆየውን የኢኮኖሚ ቀውስ በአግባቡ አልፈቱትም በማለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ኘሬዝደንቱ ስልጣን እንዲለቁ ሲጠይቁ ነበር።