ቻይና አሜሪካ የቀዝቃዛው ጦርነት እሳቤን እንዲታቆም ጠይቃለች
አሜሪካ አሁን ላይ ቻይና እና ሩሲያ ጋር ያላቸው አጋርነትና ወዳጅነት እንደሚያሳስባት አስታወቀች፡፡
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ይ ጋር ለአምስት ሰዓት የቆየ ውይይት አድርገዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት አንቶኒ ብሊንከን የሞስኮ እና የቤጅንግ አጋር መሆን እንደሚሳስባት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ በኢንዶኔዥያ የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ሲጠናቀቅ ነው ተገናኝተው መወያየታቸው የተገለጸው፡፡ አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸውና አጋሮቿ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ሩሲያን ማውገዛቸውን ጠቅሰው ቻይናም ይህንን እንድትቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ በበኩላቸው አሜሪካ ሀገራቸውን ለማጥቃት ከማሰብ እንድትቆጠብ መጠየቃቸውም ነው ተገለጸው፡፡ ዋሸንግተን፤ የቀዝቃዛው ዓለም ጦርነት እሳቤን ከመናፈቅ እንድትቆጠብ እና የቤጅንግን የውጭ እና የውስጥ ፖሊሲዎች እድታከብርም ነው የቻይናው ሚኒስትር የጠየቁት፡፡
አሜሪካ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን እንዲታነሳም የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተሰምቷል፡፡ አንቶኒ ብሊንከን፤ የቻይናውን አቻቸውን ቤጅንግ ለምን በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል ተቃወመች የሚል ጥያቄ እንዳቀረቡም ነው የተገለጸው፡፡
የቻይና እና የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በአካል የተወያዩት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኑነት በተካረረበትና ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በገባበት ወቅት ነው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሀገራቸው ወታደሮች ቻይና በታይዋን ላይ የምታደርገውን ሁሉ እንደሚዋጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡