ፖለቲካ
የቦኮሃራም ወረራን ተከትሎ የካሜሩን መከላከያ ሚኒስትር ወደ ሰሜናዊ ግዛት በረሩ
ቦኮሀራም በግዛቱ ሁለት ወታደራዊ የጦር ሰፈሮችን በመውረር ቢያንስ 13 የመንግስት ሃይሎችን ገድሏል ብለዋል ሚኒስትሩ
በረራው የካሜሩን ጦር ኃይል ቃል አቀባይ የሽብር ቡድኑ በግዛቱ “የውስጥ ተሃድሶ” አድርጎ በሙሉ ኋይሉ መመለሱን መናገራቸውን ተከትሎ ነው
የካሜሩን የመከላከያ ሚኒስትር ጆሴፍ ቤቲ አሶሞ በቦኮ ሃራም በተደጋጋሚ የሚደርሱ ጥቃቶችን ተከትሎ ወደ ሀገሪቱ ሩቅ ሰሜን ክልል ገብተዋል፡፡
የአሶሞ ጉብኝት የመጣው የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ ሲረልሌ ሰርጌ አታንፋክ ጉሞ የሽብር ቡድኑ “የውስጥ ተሃድሶ” ን ተከትሎ በክልሉ “ሙሉ ኃይል” መመለሱን ከገለጸ ከአንድ ቀን በኋላ ነው ፡፡ አሶሞ ለሁለት ቀናት ሁኔታውን በመገምገም የአማፅያን ጥቃት ለሚገጥሙ ኃይሎች ድጋፍ ይሰጣል ፡፡
“ጉብኝቱ ነዋሪዎችን ለመጠበቅ እንዲሁም የሩቅ ሰሜን ክልል የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ ለማድረግ የተደረጉ ክዋኔዎችን ለማጣራት ያለመ ነው” ሲል የመከላከያ ሰራዊት መግለጫው አመልክቷል ፡፡
የቦኮ ሀራም ታጣቂዎች ባለፉት አራት ቀናት በክልሉ ሁለት ወታደራዊ የጦር ሰፈሮችን በመውረር ቢያንስ 13 የመንግስት ሃይሎችን መገደላቸውን የመከላከያ ሰራዊቱ አስታውቋል፡፡ የካሜሮን ጦር “በብርቱ እና በብቃት” የበቀል እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ጉሞ ማክሰኞ ተናግረዋል፡፡