የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከማዳጋስካር ጋር ጨዋታ ያደርጋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማዳጋስካር እና ኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከማዳጋስካር እና መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በአቢጃን ከኮትዲቯር አቻው ጋር ጨዋታ ያደርጋል፡፡ አሰልጣኙ ለነዚህ ጨዋታዎች ዝግጅታቸውንም መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በባሕር ዳር እንደሚጀምሮ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረገጹ አስነብቧል፡፡
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች፡-
1. ተክለማሪያም ሻንቆ - ከኢትዮጵያ ቡና
2. ጀማል ጣሰው - ከወልቂጤ ከተማ
3. ፍሬው ጌታሁን - ከድሬዳዋ ከተማ
4. ምንተስኖት አሉ - ከሰበታ ከተማ
5. አስቻለው ታመነ - ከቅዱስ ጊዮርጊስ
6. ቶማስ ስምረቱ - ከወልቂጤ ከተማ
7. ያሬድ ባዬ - ከፋሲል ከነማ
8. መናፍ አወል - ከባሕር ዳር ከተማ
9. ረመዳን የሱፍ - ከወልቂጤ ከተማ
10. ሱሌማን ሀሚድ - ከሀዲያ ሆሳዕና
11. አስራት ቱንጆ - ከኢትዮጵያ ቡና
12. ጋዲሳ መብራቴ - ከቅዱስ ጊዮርጊስ
13. አማኑኤል ዮሃንስ - ከኢትዮጵያ ቡና
14. አብዱከሪም ወርቁ - ከወልቂጤ ከተማ
15. ፍፁም አለሙ - ከባሕርዳር ከተማ
16. ሀብታሙ ተከስተ - ከፋሲል ከነማ
17. ሽመልስ በቀለ - ከግብጹ መስር አል ቃዲስ
18. ሀይደር ሽረፋ - ከቅዱስ ጊዮርጊስ
19. መሱድ መሀመድ - ከሰበታ ከተማ
20. ሽመክት ጉግሳ - ከፋሲል ከነማ
21. ሱራፌል ዳኛቸው — ከፋሲል ከነማ
22. ጌታነህ ከበደ – ከቅዱስ ጊዮርጊስ
23. አማኑኤል ገ/ሚካኤል— ከቅዱስ ጊዮርጊስ
24. አቡበከር ናስር— ከኢትዮጵያ ቡና
25. ሙጂብ ቃሲም - ከፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የተመረጡ ተጫዎቾች ናቸው።