ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቅ ዘመቻ ተጀመረ
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ልጃቸው ግብር አጭበርብሮ ዝም ብለዋል እና ሌሎችም ክሶች ቀርቦባቸዋል
በአሜሪካ በተያዘው ዓመት ብቻ 13 ጊዜ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አስተዳድራቸው ላይ ከስልጣን ይነሱ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል
ሪፐብሊካኖች ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከስልጣን ለማንሳት መዘቻ መጀመራቸውን ገለጹ፡፡
የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባላት ብዙዎቹ ከሪፐብሊካን እና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ተመራጮች የተያዘ ነው፡፡
የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ከስልጣን የማንሳት ስልጣን ያለው የሀገሪቱ ምክር ቤት አሁን ደግሞ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል የሪፐብሊካን ፓርቲ ተመራጮች ዘመቻ መጀመራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ልጃቸው ሀንተር ባይደን ግብር አጭበርብሯል፣ ፕሬዝዳንቱም ይህ ሲሆን ዝም ብለዋል በሚል በምክር ቤቱ አባላት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
እንዲሁም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ ድንበር በኩል የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በሚጥስ መልኩ ስደተኞች በገፍ ሲገቡ እና ሌሎች የሕግ ጥሰቶች ሲፈጸሙ ሃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል ተጨማሪ ክስ መቅረቡ ተገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከስልጣን እንዲነሱ የምክር ቤት አባላት ድምጽ እንዲሰጡ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን የሪፐብሊካን ፓርቲ ተመራጮች ተናግረዋል ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲነሱ ሁለት ሶስተኛው የምክር ቤቱ አባላት ውሳኔውን ማጽደቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ እንደማይሆን የዲሞክራት ፓርቲ ተመራጮች በመናገር ላይ እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በአሜሪካ በተያዘው 2023 ዓመት ብቻ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አስተዳድራቸው አመራሮች ላይ 13 ጊዜ ከስልጣን ይነሱ የሚሉ ዘመቻዎች የተካሄዱ ሲሆን አንዱም አልተሳካም ተብሏል፡፡