ካናዳ ታይታኒክን ለመጎብኘት ያቀናችው ሰርጓጅ ጀልባ ፍንዳታ ላይ ምርመራ ከፈተች
በታይታን ጀልባ ላይ የተሳፈሩት አምስቱ ሰዎች "አስከፊ አደጋ" ከደረሰባቸው በኋላ ህይወታቸው አልፏል
ሙሉ ምርመራው ከ18 ወራት እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ ይችላል ተብሏል
የካናዳ ባለስልጣናት ታይታኒክ መርከብ አካባቢ የወደቀችው "ታይታን" ሰርጓጅ ጀልባ ላይ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን ተናገሩ።
ሰርጎጅ ጀልባዋ ከአምስት ሰዎች ጋር በታይታኒክ ፍርስራሽ አቅራቢያ መሰወሯ ለቀናት ዓለም አቀፍ የፍለጋ እና የነፍስ የማዳን ስራ አስጀምሯል።
የሀገሪቱ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ ሊቀ-መንበር ካቲ ፎክስ "የእኛ ተልዕኮ ምን እንደተፈጠረ እና ለምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እና ለወደፊቱ እንደዚህ ያሉ ክስተቶችን እድል ወይም አደጋን ለመቀነስ ምን መለወጥ እንዳለበት ማወቅ ነው" ሲሉ ስለ ምርመራው ተናግረዋል።
"ሁሉም ሰው መልስ እንደሚፈልግ እናውቃለን፤ በተለይም ቤተሰቦች እና ህዝቡ" ብለዋል።
ሙሉ ምርመራው ከ18 ወራት እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ ይችላል ተብሏል።
የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ የትራንስፖርት ደህንነትን ለማሻሻል ዓላማ በማድረግ የአየር፣ የባቡር፣ የባህር እና የቧንቧ መስመር አደጋዎችን በየጊዜው ይመረምራል።
የአሜሪካ የባህር ጠረፍ ጥበቃ ሀሙስ እንዳስታወቀው በጀልባዋ ላይ የተሳፈሩት አምስቱ ሰዎች "አስከፊ አደጋ" ከደረሰባቸው በኋላ ህይወታቸው አልፏል።
ከታይታኒክ 500 ሜትር ርቀት ላይ ባለው የባህር ወለል ላይ የቆሻሻ ክምር ተገኝቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሮያል ካናዳ ፖሊስ የታይታን ተጓዦችን ሞት ያስከተለው ክስተት የትኛን የወንጀል ህጎች እንደተጣሰ እየተቃኘ ነው ተብሏል።
የመርማሪዎቹ ስራ ምርመራ አስፈላጊ እንዳልሆነና እንዳልሆነ መወሰን እንደሆነ ተገልጿል።